ሐዋርያት ሥራ 24:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)22 ፊልክስ ግን የመንገዱን ነገር አጥብቆ አውቆአልና “የሻለቃው ሉስዮስ በወረደ ጊዜ ነገራችሁን እቆርጣለሁ፤” ብሎ ወደ ፊት አዘገያቸው። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም22 ፊልክስ ግን የጌታን መንገድ በሚገባ ዐውቆ ስለ ነበር፣ “የጦር አዛዡ ሉስያስ ሲመጣ ለጕዳያችሁ ውሳኔ እሰጣለሁ” ብሎ ነገሩን በቀጠሮ አሳደረው። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም22 ፊልክስ ግን ስለ ክርስትና እምነት በደንብ ያውቅ ስለ ነበር “የጦር አዛዡ ሉስዮስ በመጣ ጊዜ፥ ስለ ጉዳያችሁ ውሳኔ እሰጣለሁ” ብሎ አሰናበታቸው። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)22 ፊልክስ ግን አይሁድ ከጥንት ጀምሮ የክርስቲያንን ወገኖች ሕግና ትምህርት እንደሚቃወሙ ያውቅ ነበር፤ ስለዚህም “እንኪያስ የሺ አለቃው ሉስዮስ በመጣ ጊዜ ነገራችሁን እናውቅ ዘንድ እንመረምራለን” ብሎ ቀጠራቸው። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)22 ፊልክስ ግን የመንገዱን ነገር አጥብቆ አውቆአልና፦ የሻለቃው ሉስዮስ በወረደ ጊዜ ነገራችሁን እቆርጣለሁ ብሎ ወደ ፊት አዘገያቸው። ምዕራፉን ተመልከት |