ሐዋርያት ሥራ 23:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)21 እንግዲህ አንተ በጅ አትበላቸው፤ እስኪገድሉት ድረስ እንዳይበሉና እንዳይጠጡ ተማምለው ከእነርሱ ከአርባ የሚበዙ ሰዎች ያደቡበታልና፤ አሁንም የተዘጋጁ ናቸው፤ የአንተንም ምላሽ ይጠብቃሉ፤” አለው። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም21 ስለዚህ ዕሺ አትበላቸው፤ ምክንያቱም ከመካከላቸው ከአርባ በላይ የሚሆኑት ሊገድሉት አድፍጠው እየጠበቁት ነው፤ ደግሞም እስኪገድሉት ድረስ እህል ውሃ ላለመቅመስ ተማምለዋል፤ አሁንም ተዘጋጅተው የአንተን መልስ እየተጠባበቁ ነው።” ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም21 ነገር ግን እሺ አትበላቸው፤ እርሱን ሳንገድል እህል አንበላም፤ ውሃም አንጠጣም በማለት የተማማሉ ከአርባ የሚበልጡ ሰዎች እርሱን ለመግደል አድፍጠዋል፤ አሁን እነርሱ የሚጠብቁት የአንተን መልስ ብቻ ነው።” ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)21 አንተ ግን እሽ አትበላቸው፤ ሊገድሉት ሽምቀዋልና፤ እስኪገድሉትም ድረስ እንዳይበሉና እንዳይጠጡ እንዲህ የተማማሉ ሰዎች ከአርባ ይበዛሉ፤ አሁንም እስክትልክላቸው ይጠብቃሉ እንጂ እነርሱ ቈርጠዋል።” ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)21 እንግዲህ አንተ በጅ አትበላቸው፤ እስኪገድሉት ድረስ እንዳይበሉና እንዳይጠጡ ተማምለው ከእነርሱ ከአርባ የሚበዙ ሰዎች ያደቡበታልና፤ አሁንም የተዘጋጁ ናቸው የአንተንም ምላሽ ይጠብቃሉ አለው። ምዕራፉን ተመልከት |