Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሐዋርያት ሥራ 22:28 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 የሻለቃውም መልሶ “እኔ ይህን ዜግነት በብዙ ገንዘብ አገኘሁት፤” አለ። ጳውሎስም “እኔ ግን በእርሷ ተወለድሁ፤” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 አዛዡም መልሶ፣ “እኔ ይህን ዜግነት ያገኘሁት ብዙ ገንዘብ አውጥቼ ነው” አለ። ጳውሎስም፣ “እኔ ግን ከተወለድሁ ጀምሮ ሮማዊ ነኝ” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 አዛዡም “እኔ ይህን ዜግነት የገዛሁት በብዙ ገንዘብ ነው” አለ፤ ጳውሎስም “እኔ ግን በሮም ዜግነት ተወልጄአለሁ” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 የሻ​ለ​ቃ​ውም መልሶ፥ “እኔ ይህ​ችን ዜግ​ነት ያገ​ኘ​ኋት ብዙ ገን​ዘብ ሰጥቼ ነው” አለው፤ ጳው​ሎ​ስም፥ “እኔማ የተ​ወ​ለ​ድሁ በዚ​ያው ነው” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 የሻለቃውም መልሶ፦ እኔ ይህን ዜግነት በብዙ ገንዘብ አገኘሁት አለ። ጳውሎስም፦ እኔ ግን በእርስዋ ተወለድሁ አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሐዋርያት ሥራ 22:28
4 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የሻለቃውም ቀርቦ “አንተ ሮማዊ ነህን? ንገረኝ፤” አለው፤ እርሱም “አዎን” አለ።


ስለዚህም ሊመረምሩት ያሰቡት ከእርሱ ወዲያው ተለዩ፤ የሻለቃውም ደግሞ ሮማዊ መሆኑን ባወቀ ጊዜ ፈራ፤ አሳስሮት ነበርና።


በዚያ ዘመን በዚህም ዓለም ያለ ክርስቶስ ከእስራኤል መንግሥት ርቃችሁ፥ ለተስፋውም ቃል ኪዳን እንግዶች ሆናችሁ፥ ተስፋን አጥታችሁና ከእግዚአብሔር ተለይታችሁ እንደ ነበር አስታውሱ።


እንግዲያስ ከእንግዲህ ወዲህ ከቅዱሳን ጋር ዜጎችና የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ናችሁ እንጂ ባዕዶችና መጻተኞች አይደላችሁም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች