Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሐዋርያት ሥራ 20:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ያንም አገር እያለፈ በብዙ ቃል ከመከራቸው በኋላ ወደ ግሪክ አገር መጣ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ባለፈባቸውም ስፍራዎች ሕዝቡን በብዙ ቃል እየመከረ ግሪክ አገር ደረሰ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 በእነዚያ በሚያልፍባቸው ስፍራዎች ምእመናንን በብዙ ምክር እያበረታታ ወደ ግሪክ አገር ሄደ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 በዚያ አው​ራ​ጃም አልፎ ሄደ፤ በቃ​ሉም ብዙ አስ​ተ​ማ​ራ​ቸው፤ ከዚ​ያም በኋላ ወደ ግሪክ ሀገር ሄደ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 ያንም አገር እያለፈ በብዙ ቃል ከመከራቸው በኋላ ወደ ግሪክ አገር መጣ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሐዋርያት ሥራ 20:2
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እንግዲህ በቀረውስ ወንድሞች ሆይ! እግዚአብሔርን ለማስደሰት እንዴት መመላለስ እንደሚገባችሁ ከእኛ ዘንድ ተቀብላችኋል፤ በእርግጥም እየተመላለሳችሁ ነው፤ ከዚህም በበለጠ አብዝታችሁ እንድታደርጉት በጌታ በኢየሱስ እንለምናችኋለን፤ እንመክራችኋለንም።


ምክራችን ከስሕተት ወይም ከርኩሰት ከተንኰልም የመነጨ አልነበረምና፤


እኛም በክርስቶስ ፍጹም አድርገን ሁሉንም ሰው ለማቅረብ ሁሉንም ሰው እየገሠጽንና ሁሉንም ሰው በጥበብ ሁሉ እያስተማርን የምንሰብከው እርሱ ነው፤


አባት ለልጁ እንደሚሆነው እኛም እንዴት ለእያንዳንዳችሁ እንደ ሆንን እናንተው ታውቁታላችሁ፥


ወጥቶም እንጀራ ቆርሶም በላ፤ ብዙ ጊዜም እስኪ ነጋ ድረስ ተነጋገረ እንዲህም ሄደ።


ወዲያውም ወንድሞች ጳውሎስንና ሲላስን በሌሊት ወደ ቤርያ ሰደዱአቸው፤ በደረሱም ጊዜ ወደ አይሁድ ምኵራብ ገቡ፤


በአንፊጶሊስና በአጶሎንያም ካለፉ በኋላ ወደ ተሰሎንቄ መጡ፤ በዚያም የአይሁድ ምኵራብ ነበረ።


ከዚያም ወደ ፊልጵስዩስ ደረስን፤ እርሷም የመቄዶንያ ከተማ ሆና የወረዳ ዋና ከተማና ቅኝ አገር ናት፤ በዚህችም ከተማ አንዳንድ ቀን እንቀመጥ ነበር።


አብያተ ክርስትያናትንም እያጸና በሶርያና በኪልቅያ ይዞር ነበር።


በብዙ ሌላ ቃልም መሰከረና “ከዚህ ጠማማ ትውልድ ዳኑ፤” ብሎ መከራቸው።


ይሁዳን እንደ ደጋኔ አጥፌዋለሁ፥ ኤፍሬምንም ቀስቱን አድርጌ አዘጋጅቻለሁ፤ ጽዮን ሆይ፥ ልጆችሽን በግሪክ ልጆች ላይ አስነሣለሁ፥ እንደ ተዋጊ ሰይፍም አደርግሻለሁ።


ስለዚህ ለሕዝቡ ሌሎች ብዙ ምክሮችን እየሰጠ መልካም ዜናን ያበሥር ነበር፤


ሁከቱም ከቀረ በኋላ ጳውሎስ ደቀ መዛሙርቱን አስመጥቶ መከራቸው፤ ተሰናብቶአቸውም ወደ መቄዶንያ ይሄድ ዘንድ ወጣ።


በዚያም ሦስት ወር ተቀምጦ ወደ ሶርያ በመርከብ ሊሄድ ባሰበ ጊዜ፥ አይሁድ ሤራ ስላደረጉበት በመቄዶንያ አልፎ ይመለስ ዘንድ ቆረጠ።


ነገር ግን ጌታ ቢፈቅድ ፈጥኜ ወደ እናንተ እመጣለሁ፤ የትዕቢተኞችንም ኃይል አውቃለሁ እንጂ ቃላቸውን አይደለም፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች