Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ሐዋርያት ሥራ 20:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ጳውሎስም ወርዶ በላዩ ወደቀ፤ አቅፎም “ነፍሱ አለችበትና አትንጫጩ፤” አላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ጳውሎስም ወርዶ በላዩ ተጋድሞ ዐቀፈውና፣ “ሕይወቱ በውስጡ ስላለች ሁከት አትፍጠሩ!” አላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ነገር ግን ጳውሎስ ወርዶ በልጁ ላይ ጐንበስ በማለት አቀፈውና “ገና በሕይወት አለ፤ አትደንግጡ!” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ጳው​ሎ​ስም ወርዶ በላዩ ወደቀ፤ አቅ​ፎም ያዘው፤ እነ​ር​ሱ​ንም፥ “ነፍሱ አለ​ችና አት​ደ​ን​ግጡ” አላ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ጳውሎስም ወርዶ በላዩ ወደቀ፥ አቅፎም፦ ነፍሱ አለችበትና አትንጫጩ አላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሐዋርያት ሥራ 20:10
8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ወደ ውስጥ ገብቶም፥ “ይህን ያህል ለምን ትታወካላችሁ ለምን ታለቅሳላችሁ? ልጅቱ ተኝታለች እንጂ አልሞተችም” አላቸው።


ጌታም ባያት ጊዜ ራራላትና፦ “አታልቅሽ፤” አላት።


ይህንንም ከተናገረ በኋላ “ወዳጃችን አልዓዛር ተኝቶአል፤ ነገር ግን ከእንቅልፉ ላስነሣው እሄዳለሁ፤” አላቸው።


ኢየሱስ “ካመንሽ የእግዚአብሔርን ክብር እንደምታዪ አልነገርሁሽምን?” አላት።


አውጤኪስ የሚሉትም አንድ ጎበዝ በመስኮት ተቀምጦ ታላቅ እንቅልፍ አንቀላፍቶ ነበር፤ ጳውሎስም ነገርን ባስረዘመ ጊዜ እንቅልፍ ከብዶት ከሦስተኛው ደርብ ወደ ታች ወደቀ፤ ሞቶም አነሡት።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች