ሐዋርያት ሥራ 17:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)18 ከኤፊቆሮስ ወገንና ኢስጦኢኮችም ከተባሉት ፈላስፎች አንዳንዶቹ ከእርሱ ጋር ተገናኙ። አንዳንዶቹም “ይህ ለፍላፊ ምን ሊናገር ይወዳል?” አሉ፤ ሌሎችም የኢየሱስንና የትንሣኤውን ወንጌል ስለ ሰበከላቸው “አዲሶችን አማልክት የሚያወራ ይመስላል፤” አሉ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም18 ከኤፊቆሮስና ከኢስጦኢክ የፍልስፍና ወገን የሆኑትም ወደ እርሱ መጥተው ይከራከሩት ነበር። አንዳንዶቹ፣ “ይህ ለፍላፊ ምን ለማለት ይፈልጋል?” ይሉ ነበር፤ ሌሎች ደግሞ ስለ ኢየሱስና ስለ ትንሣኤው የምሥራች ሲሰብክ ሰምተው፣ “ስለ አዳዲስ ባዕዳን አማልክት የሚናገር ይመስላል” አሉ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም18 ኤፒኮሮሶችና እስቶይኮች የተባሉ ፈላስፎችም ወደ እርሱ እየመጡ ይከራከሩ ነበር። አንዳንዶቹ “ይህ ለፍላፊ ምን ማለት ይፈልጋል?” ሲሉ፥ ሌሎች ደግሞ “ስለ አዳዲስ አማልክት የሚናገር ይመስላል” ይሉ ነበር፤ ይህንንም ያሉበት ምክንያት ጳውሎስ የኢየሱስንና የትንሣኤውን መልካም ዜና ስላበሠረ ነው። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)18 የኤፌቆሮስን ትምህርት ከተማሩ ፈላስፋዎች መካከልና ረዋቅያውያን ከሚባሉት ወገን የሆኑ ሌሎች ፈላስፎችም የተከራከሩት ነበሩ፤ እኩሌቶችም፥ “ይህ ለፍላፊ ምን ሊናገር ይፈልጋል?” ይሉ ነበር፤ ሌሎችም፥ “ስለ ኢየሱስ ከሙታን ስለ መነሣቱም ሰብኮላቸዋልና የአዲስ አምላክ ትምህርትን ያስተምራል” አሉ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)18 ከኤፊቆሮስ ወገንና ኢስጦኢኮችም ከተባሉት ፈላስፎች አንዳንዶቹ ከእርሱ ጋር ተገናኙ። አንዳንዶቹም፦ ይህ ለፍላፊ ምን ሊናገር ይወዳል? አሉ፤ ሌሎችም የኢየሱስንና የትንሣኤውን ወንጌል ስለ ሰበከላቸው፦ አዲሶችን አማልክት የሚያወራ ይመስላል አሉ። ምዕራፉን ተመልከት |