Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሐዋርያት ሥራ 17:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ጳውሎስን የሸኙት ግን እስከ አቴና አደረሱት፤ እንደሚቻላቸውም በፍጥነት ወደ እርሱ ይመጡ ዘንድ ወደ ሲላስና ወደ ጢሞቴዎስ ትእዛዝ ተቀብለው ሄዱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ጳውሎስን የሸኙት ሰዎችም አቴና አደረሱት፤ ከዚያም ሲላስና ጢሞቴዎስ ወደ እርሱ በፍጥነት እንዲመጡ የሚል ትእዛዝ ተቀብለው ተመለሱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ጳውሎስን የሸኙት ሰዎች እስከ አቴና አደረሱት “ሲላስና ጢሞቴዎስ ሳይዘገዩ በቶሎ ወደ እኔ ይምጡልኝ” የሚለውንም የጳውሎስን ትእዛዝ ይዘው ወደ ቤርያ ተመለሱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ጳው​ሎ​ስን የሸ​ኙት ሰዎ​ችም እስከ አቴና ከተማ ድረስ አብ​ረ​ውት መጥ​ተው ነበ​ርና ፈጥ​ነው ይከ​ተ​ሉት ዘንድ ወደ ሲላ​ስና ወደ ጢሞ​ቴ​ዎስ ላካ​ቸው፤ ተመ​ል​ሰ​ውም ሄዱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ጳውሎስን የሸኙት ግን እስከ አቴና አደረሱት፥ እንደሚቻላቸውም በፍጥነት ወደ እርሱ ይመጡ ዘንድ ወደ ሲላስና ወደ ጢሞቴዎስ ትእዛዝ ተቀብለው ሄዱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሐዋርያት ሥራ 17:15
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ስለዚህ ወደ ፊት ለመታገስ ባልተቻለን ጊዜ፥ በአቴና ብቻችንን ልንቀር በጎ ፈቃዳችን ሆነ።


ሲላስና ጢሞቴዎስም ከመቄዶንያ በወረዱ ጊዜ፥ ጳውሎስ ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ እንደሆነ ለአይሁድ እየመሰከረ ለቃሉ ይተጋ ነበር።


ከዚህም በኋላ ጳውሎስ ከአቴና ወጥቶ ወደ ቆሮንቶስ መጣ።


አርጢሞንን ወይም ቲኪቆስን ወደ አንተ ስልክ፥ ወደ ኒቆጵልዮን ወደ እኔ እንድትመጣ የተቻለህን ሁሉ አድርግ፤ እኔ ክረምቱን በዚያ ለማሳለፍ ወስኛለሁና።


የአቴና ሰዎች ሁሉና በዚያ የኖሩ እንግዶች አዲስ ነገርን ከመናገርና ከመስማት በቀር በሌላ ጉዳይ አይውሉም ነበርና።


ጳውሎስም በአቴና ሲጠብቃቸው ሳለ፥ በከተማው ጣዖት መሙላቱን እየተመለከተ መንፈሱ ተበሳጨበት።


ቤተ ክርስቲያኑም በመንገድ እየረዳቸው እነርሱ የአሕዛብን መመለስ እየተረኩ በፊንቄና በሰማርያ አለፉ፤ ወንድሞችንም ሁሉ እጅግ ደስ አሰኙአቸው።


በዚያን ጊዜም ወንድሞች ወዲያው ጳውሎስን እስከ ባሕር ድረስ ይሄድ ዘንድ ሰደዱት፤ ሲላስና ጢሞቴዎስም በዚያው ቀሩ።


ጳውሎስም በአርዮስፋጎስ መካከል ቆሞ እንዲህ አለ፦ “የአቴና ሰዎች ሆይ! እናንተ በሁሉ ነገር አማልክትን እጅግ እንደምትፈሩ እመለከታለሁ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች