Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሐዋርያት ሥራ 17:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ወዲያውም ወንድሞች ጳውሎስንና ሲላስን በሌሊት ወደ ቤርያ ሰደዱአቸው፤ በደረሱም ጊዜ ወደ አይሁድ ምኵራብ ገቡ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ወንድሞችም ወዲያው ጳውሎስንና ሲላስን በሌሊት ወደ ቤርያ ሰደዷቸው፤ እነርሱም እዚያ በደረሱ ጊዜ፣ ወደ አይሁድ ምኵራብ ገቡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ወንድሞች በቶሎ ጳውሎስንና ሲላስን በሌሊት ወደ ቤርያ እንዲሄዱ አደረጉአቸው፤ እዚያም በደረሱ ጊዜ ወደ አይሁድ ምኲራብ ገቡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ወን​ድ​ሞች ግን ጳው​ሎ​ስ​ንና ሲላ​ስን በሌ​ሊት ወደ ቤርያ ሸኙ​አ​ቸው፤ ወደ​ዚ​ያም በደ​ረሱ ጊዜ ወደ አይ​ሁድ ምኵ​ራብ ገቡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ወዲያውም ወንድሞች ጳውሎስንና ሲላስን በሌሊት ወደ ቤርያ ሰደዱአቸው፥ በደረሱም ጊዜ ወደ አይሁድ ምኵራብ ገቡ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሐዋርያት ሥራ 17:10
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ነገር ግን እንደምታውቁት በፊልጵስዩስ አስቀድመን መከራንና እንግልትን ብንቀበልም እንኳ፥ በታላቅም ተቃውሞ ፊት የእግዚአብሔርን የምሥራች ቃል ለእናንተ ለመናገር በአምላካችን ድፍረትን አገኘን።


ጳውሎስም እንደ ልማዱ ወደ እነርሱ ገባ፤ ሦስት ሰንበትም ያህል ከእነርሱ ጋር ከመጻሕፍት እየጠቀሰ ይነጋገር ነበር፤


የሸኙትም የቤርያው ሶጳጥሮስ ከተሰሎንቄ ሰዎችም አርስጥሮኮስና ሲኮንዱስ የደርቤኑም ጋይዮስና ጢሞቴዎስ የእስያ ሰዎችም ቲኪቆስ ጥሮፊሞስም ነበሩ፤


ደቀ መዛሙርት ግን በሌሊት ወስደው በቅጥር ላይ አሳልፈው በቅርጫት አወረዱት።


ዮናታንም ዳዊትን፤ “ ‘በአንተና በእኔ፥ በዘሮችህና በዘሮቼ መካከል ጌታ ለዘለዓለም ምስክር ነው’ ተባብለን ወዳጅነታችን እንዲጸና በጌታ ስም ስለ ተማማልን እንግዲህ በሰላም ሂድ” አለው። ከዚያም ዳዊት ተነሥቶ ሄደ፤ ዮናታንም ወደ ከተማ ተመለሰ።


በዚህም ወራት ጴጥሮስ መቶ ሃያ በሚያህል በሰዎች ማኅበር አብረው በነበሩ በወንድሞቹ መካከል ተነሥቶ አለ


ወዲያውም ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ እርሱ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ በምኵራቦቹ ሰበከ።


ያንጊዜ ሐዋርያትና ሽማግሌዎች ከቤተ ክርስቲያኑ ሁሉ ጋር ከእነርሱ የተመረጡትን ሰዎች ከጳውሎስና ከበርናባስ ጋር ወደ አንጾኪያ ይልኩ ዘንድ ፈቀዱ፤ እነርሱም በወንድሞች መካከል ዋናዎች ሆነው በርስያን የተባለው ይሁዳና ሲላስ ነበሩ።


በአንፊጶሊስና በአጶሎንያም ካለፉ በኋላ ወደ ተሰሎንቄ መጡ፤ በዚያም የአይሁድ ምኵራብ ነበረ።


ከእነርሱም አንዳንዶቹ ተረድተው ከሚያመልኩም ከግሪክ ሰዎች ብዙ ከከበሩትም ሴቶች ጥቂቶች ያይደሉ፥ ከጳውሎስና ከሲላስ ጋር ተባበሩ።


ባላገኙአቸውም ጊዜ ኢያሶንንና ከወንድሞች አንዳንዶችን ወደ ከተማው አለቆች ጎትተው “ዓለምን ያወኩ እነዚህ ወደዚህ ደግሞ መጥተዋል፥ ኢያሶንም ተቀብሎአቸዋል፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች