Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ሐዋርያት ሥራ 15:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 “‘ከዚህ በኋላ እመለሳለሁ፤ የፈረሰውን የዳዊትን ቤት እገነባለሁ። ፍርስራሹን መልሼ አቆማለሁ፤ እንደገናም እሠራዋለሁ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 “ ‘ከዚህ በኋላ እመለሳለሁ፤ የወደቀውን የዳዊትን ቤት እገነባለሁ። ፍርስራሹን መልሼ አቆማለሁ፤ እንደ ገናም እሠራዋለሁ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ‘ከዚህ በኋላ እመለሳለሁ፤ የፈረሰውንም የዳዊትን ቤት እሠራለሁ፤ ፍርስራሹንም ጠግኜ እንደገና አቆማለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ከዚ​ህም በኋላ የወ​ደ​ቀ​ች​ውን የዳ​ዊ​ትን ቤት መልሼ እሠ​ራ​ታ​ለሁ፤ ፍራ​ሽ​ዋ​ንም አድ​ሳ​ለሁ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16-17 ‘ከዚህ በኋላ የቀሩት ሰዎችና በስሜ የተጠሩት አሕዛብ ሁሉ ጌታን ይፈልጉ ዘንድ እመለሳለሁ፥ የወደቀችውንም የዳዊትን ድንኳን እንደ ገና እሠራታለሁ፥ ፍራሽዋንም እንደ ገና እሠራታለሁ እንደ ገናም አቆማታለሁ ይላል ይህን የሚያደርግ ጌታ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሐዋርያት ሥራ 15:16
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሕዝቡ፥ ንጉሥ ሮብዓም ጥያቄውን እንዳልተቀበለው በተገነዘበ ጊዜ “ከዳዊት ጋር ምን ድርሻ አለን? ከእሴይ ልጅ ከዳዊት ጋር ምን ርስት አለን፤ የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! ወደየድኳንኖችህ ሂድ! ዳዊት ሆይ የራስህን ቤት ጠብቅ!” ብለው መለሱለት። ስለዚህ የእስራኤል ሕዝብ ወደየቤቱ ሄደ።


ከነቀልኋቸውም በኋላ መልሼ እምራቸዋለሁ፥ እያንዳንዱንም ወደ ርስቱ እያንዳንዱንም ወደ ምድሩ እመልሳለሁ።


በምድርም ሁሉ ላይ ሁለት ሦስተኛው ተቈርጠው ይጠፋሉ፥ ይላል ጌታ፤ አንድ ሦስተኛው ክፍልም በእርሷ ይቀራል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች