ሐዋርያት ሥራ 13:33 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)33 ይህን ተስፋ እግዚአብሔር በሁለተኛው መዝሙር ደግሞ “አንተ ልጄ ነህ፤ እኔ ዛሬ ወለድሁህ፤” ተብሎ እንደ ተጻፈ፥ ኢየሱስን አስነሥቶ ለእኛ ለልጆቻቸው ፈጽሞአልና። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም33 ኢየሱስንም ከሙታን በማስነሣቱ ለእነርሱ የገባውን ቃል ለእኛ ለልጆቻቸው ፈጽሟል፤ ይኸውም እግዚአብሔር በሁለተኛው መዝሙር እንዲህ ብሎ ተጽፏል፤ “ ‘አንተ ልጄ ነህ፤ እኔ ዛሬ ወለድሁህ።’ ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም33 እግዚአብሔር ኢየሱስን ከሞት በማስነሣቱ ይህንኑ ተስፋ ለእኛ ለልጆቻቸው ፈጽሞታል፤ ይህም በሁለተኛው መዝሙር፥ ‘አንተ ልጄ ነህ፥ እኔ ዛሬ ወልጄሃለሁ፤’ ተብሎ እንደ ተጻፈው ነው። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)33 በሁለተኛው መዝሙር፦ ‘አንተ ልጄ ነህ፤ እኔ ዛሬ ወለድሁህ’ እንዳለ ኢየሱስን አስነሥቶ ተስፋውን ለእኛ ለልጆቻቸው ፈጽሞአል። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)33 ይህን ተስፋ እግዚአብሔር በሁለተኛው መዝሙር ደግሞ፦ ‘አንተ ልጄ ነህ እኔ ዛሬ ወለድሁህ’ ተብሎ እንደ ተጻፈ፥ ኢየሱስን አስነሥቶ ለእኛ ለልጆቻቸው ፈጽሞአልና። ምዕራፉን ተመልከት |