Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሐዋርያት ሥራ 13:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 እርሱንም ከሻረው በኋላ ዳዊትን በእነርሱ ላይ እንዲነግሥ አስነሣው፤ ሲመሰክርለትም ‘እንደ ልቤ የሆነ ሰው ፈቃዴንም ሁሉ የሚያደርግ የእሴይን ልጅ ዳዊትን አገኘሁ፤’ አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ሳኦልንም ከሻረው በኋላ፣ ዳዊትን አነገሠላቸው፤ እግዚአብሔርም ስለ እርሱ፣ ‘እንደ ልቤ የሆነና እኔ የምሻውን ሁሉ የሚያደርግ የእሴይን ልጅ ዳዊትን አገኘሁ’ ሲል መሰከረለት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ሳኦልንም ከሻረው በኋላ ዳዊትን አነገሠላቸው፤ እግዚአብሔር ስለ ዳዊት ሲመሰክር፦ ‘እንደ ፍላጎቴ የሚሆንልኝን፤ ፈቃዴንም የሚፈጽመውን፥ የእሴይን ልጅ ዳዊትን አገኘሁ’ ብሎአል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 እር​ሱ​ንም ሻረው፤ ከእ​ር​ሱም በኋላ ዳዊ​ትን አነ​ገ​ሠ​ላ​ቸው፤ ‘የእ​ሴ​ይን ልጅ ዳዊ​ትን ፈቃ​ዴን ሁሉ የሚ​ፈ​ጽም እንደ ልቤም የታ​መነ ሰው ሆኖ አገ​ኘ​ሁት’ ብሎ መሰ​ከ​ረ​ለት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 እርሱንም ከሻረው በኋላ ዳዊትን በእነርሱ ላይ እንዲነግሥ አስነሣው፥ ሲመሰክርለትም፦ እንደ ልቤ የሆነ ሰው ፈቃዴንም ሁሉ የሚያደርግ የእሴይን ልጅ ዳዊትን አገኘሁ አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሐዋርያት ሥራ 13:22
32 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ጌታ ይህን ያደረገበት ምክንያት ዳዊት በሒታዊው ኦርዮን ላይ ከፈጸመው ኃጢአት በቀር ጌታን ደስ የሚያሰኝ ነገር በማድረጉና ትእዛዙንም በብርቱ ጥንቃቄ በመጠበቁ ነው።


ሳሙኤልም የዘይቱን ቀንድ ወስዶ በወንድሞቹ ፊት ቀባው። ከዚያ ቀን ጀምሮ የጌታ መንፈስ በዳዊት ላይ በኃይል መጣ፤ ሳሙኤልም ወደ ራማ ተመለሰ።


ጌታ ሳሙኤልን፥ “በእስራኤል ላይ እንዳይነግሥ ለናቅሁት ለሳኦል የምታለቅስለት እስከ መቼ ነው? ወደ ቤተልሔሙ ሰው ወደ እሴይ ስለምልክህ፥ ዘይት በቀንድ ሞልተህ ሂድ፤ ከልጆቹ አንዱ ንጉሥ ይሆን ዘንድ መርጬዋለሁ” አለው።


ሳሙኤልም እንዲህ አለው፤ “ጌታ የእስራኤልን መንግሥት ዛሬ ከአንተ ቀዶታል፤ ከአንተም ለሚሻል ለጎረቤትህ አሳልፎ ሰጥቶታል።


ሳሙኤል ግን ሳኦልን፥ “ከአንተ ጋር አልመለስም፤ አንተ የጌታን ቃል ንቀሃል፤ ጌታም በእስራኤል ላይ ንጉሥ እንዳትሆን ንቆሃል” አለው።


እርሱም በእግዚአብሔር ፊት ሞገስ አግኝቶ ለያዕቆብ አምላክ ማደሪያን ያገኝ ዘንድ ለመነ።


አቢያም፥ እንደ ታላቁ አያቱ እንደ ዳዊት በጌታ ዘንድ ፍጹም ታማኝ ሆኖ በመገኘት ፈንታ፥ አባቱ ሮብዓም ይፈጽመው የነበረውን ኃጢአት ሁሉ መሥራቱን ቀጠለ።


አሁንም አገልጋዬን ዳዊትን እንዲህ በለው፤ ‘የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፤ በሕዝቤ በእስራኤል ላይ ገዥ እንድትሆን ከሜዳ አነሣሁህ፤ ከበግ ጥበቃም ወሰድሁህ፤


የይሁዳም ሰዎች ወደ ኬብሮን መጡ፤ በዚያም ዳዊትን ቀብተው በይሁዳ ቤት ላይ አነገሡት። ሳኦልን የቀበሩት የያቤሽ ገለዓድ ሰዎች መሆናቸውን ለዳዊት በነገሩት ጊዜ፥


ዐመፅ እንደ ሟርተኛነት ያለ ኃጢአት፥ እልኸኝነትም እንደ ጣዖት አምልኮ ያለ ክፉ ነገር ነው፤ አንተ የጌታን ቃል ንቀሃልና እርሱም ንጉሥ እንዳትሆን ንቆሃል።”


ልብንም የሚያውቅ አምላክ ለእኛ ደግሞ እንደ ሰጠን መንፈስ ቅዱስን በመስጠት መሰከረላቸው፤


ከዚያም በኋላ የእስራኤል ልጆች ተመልሰው አምላካቸውን ጌታንና ንጉሣቸውን ዳዊትን ይፈልጋሉ፤ በኋለኛውም ዘመን ፈርተው ወደ ጌታና ወደ መልካምነቱ ይመጣሉ።


በአብርሃምና በይስሐቅ በያዕቆብም ዘር ላይ ገዦች እንዲሆኑ ከዘሩ ላለመውሰድ፥ የያዕቆብንና የባርያዬን የዳዊትን ዘር እኔ ደግሞ እጥላለሁ። እኔ ምርኮአቸውን እመልሳለሁና፥ እምራቸዋለሁምና።”


እኔ ግን ንጉሤን ሾምሁ በተቀደሰው ተራራዬ በጽዮን ላይ።


እንዲሁ ሳኦል በጌታ ላይ ስላደረገው ኃጢአት፥ የጌታንም ቃል ስላልጠበቀ ሞተ። ደግሞም መናፍስት ጠሪ ስለ ጠየቀ፥


ከአንተ በፊት ካስወገድሁት ከሳኦል ምሕረቴን እንዳራቅሁ ከእርሱ ግን አላርቅም።


ሳኦልና ሦስቱ ልጆቹ፥ አብረውት የነበሩ ሰዎች ሁሉና ጋሻ ጃግሬው የሞቱት በዚያኑ ቀን ነበር።


“እኔን ከመከተል ተመልሶአልና፥ ትእዛዜንም አልፈጸመምና፥ ሳኦልን በማንገሤ ተጸጽቻለሁ።” ሳሙኤልም እጅግ ተቆጥቶ፥ ሌሊቱን ሁሉ ወደ ጌታ ጮኸ።


በክፉ ሥራችሁ ብትጸኑ ግን፥ እናንተም ንጉሣችሁም ትጠፋላችሁ።”


በላያቸውም አንድ እረኛ አቆማለሁ እርሱም ያሰማራቸዋል፥ እርሱም ባርያዬ ዳዊት ነው፤ ያሰማራቸዋል እረኛም ይሆናቸዋል።


በዙፋኑ ላይ የሚነግሥ ልጅ እንዳይሆንለት ከአገልጋዬ ከዳዊት ጋር፥ ከአገልጋዮቼም ከሌዋውያን ካህናት ጋር ያለው ቃል ኪዳኔ ደግሞ ይፈርሳል።


ሳሙኤልም እንዲህ አለ፤ “ታዲያ ጌታ ከራቀህ፥ ጠላትም ከሆነህ ለምን እኔን ትጠይቀኛለህ?


ዳዊትም በራሱ ዘመን የእግዚአብሔርን አሳብ ካገለገለ በኋላ አንቀላፋ፤ ከአባቶቹም ጋር ተጨምሮ መበስበስን አየ፤


ቦዔዝም ኢዮቤድን ወለደ፥ ኢዮቤድም እሴይን ወለደ፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች