Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ሐዋርያት ሥራ 12:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ጴጥሮስም ወደ ልቡ ተመልሶ “ጌታ መልአኩን ልኮ ከሄሮድስ እጅና የአይሁድ ሕዝብ ይጠብቁት ከነበረው ሁሉ እንደ አዳነኝ አሁን በእውነት አወቅሁ፤” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ጴጥሮስም ሲረጋጋ፣ “ጌታ መልአኩን ልኮ ከሄሮድስ እጅና አይሁድ ካሰቡብኝ ሁሉ እንዳወጣኝ አሁን ያለ ጥርጥር ዐወቅሁ” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ጴጥሮስም ወደ ልቡናው ተመልሶ፥ “ጌታ መልአኩን ልኮ ከሄሮድስ እጅና የአይሁድ ሕዝብ ይጠባበቁት ከነበረው ነገር ሁሉ ያዳነኝ መሆኑን አሁን ገና በእውነት ዐወቅሁ!” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ያን​ጊ​ዜም የጴ​ጥ​ሮስ ልቡና ተመ​ለ​ሰ​ለ​ትና፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አ​ኩን ልኮ ከሄ​ሮ​ድስ እጅና የአ​ይ​ሁድ ሕዝብ ይጠ​ብ​ቁት ከነ​በ​ረው ሁሉ እንደ አዳ​ነኝ በእ​ው​ነት አሁን ዐወ​ቅሁ” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ጴጥሮስም ወደ ልቡ ተመልሶ፦ “ጌታ መልአኩን ልኮ ከሄሮድስ እጅና የአይሁድ ሕዝብ ይጠብቁት ከነበረው ሁሉ እንደ አዳነኝ አሁን በእውነት አወቅሁ” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሐዋርያት ሥራ 12:11
27 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አብራምንም አለው፦ “ዘርህ ለእርሱ ባልሆነች ምድር ስደተኞች እንደሚሆኑ በእርግጥ እወቅ፥ ባርያዎች አድርገውም አራት መቶ ዓመት ያስጨንቋቸዋል።


እግዚአብሔርም አብርሃምን አለው፦ “ካረጀሁ በኋላ በውኑ እወልዳለሁን? ስትል ሣራ ለምን ሳቀች?


አቢሜሌክም ይስሐቅን ጠራ እንዲህም አለው፦ “እነሆ ሚስትህ ናት፥ እንዴትስ እርሷን፦ ‘እኅቴ ናት’ አልህ?” ይስሐቅም፦ “በእርሷ ምክንያት እንዳልሞት ብዬ ነው” አለው።


ጌታ ከጠላቶቹ ሁሉና ከሳኦልም እጅ በታደገው ጊዜ፥ ዳዊት የዚህን መዝሙር ቃል ለጌታ ዘመረ፤


ጌታ ልቡ በእርሱ ዘንድ ፍጹም የሆነውን ለማጽናት ዐይኖቹ በምድር ሁሉ ይመለከታሉና። እንግዲህ አሁን የሞኞችን ተግባር ፈጽመሃል። ስለዚህም ከዛሬ ጀምሮ ጦርነት ይደረግብሃል።”


በድንኳኔ ሥር የሚኖሩ ሰዎች፦ ‘በሥጋ ያልጠገበ ማን ይገኛል?’ ይሉ የለምን?


ከስድስት ችግሮች ያድንሃል፥ በሰባተኛውም ውስጥ ክፋት አትነካህም።


ነፍሱን ከሚያሳድዱአት ያድን ዘንድ ከድሀ በኩል ቆሞአልና።


እነሆ፥ የጌታ ዐይኖች ወደሚፈሩት ናቸው፥ በቸርነቱም ወደሚታመኑ፥


ነፍሳቸውን ከሞት ያድን ዘንድ፥ በራብም ጊዜ በሕይወት ይጠብቃቸው ዘንድ።


ክፉዎቹን ክፋት ይገድላቸዋል ጻድቃንንም የሚጠሉ ይፈረድባቸዋል።


ይህ ችግረኛ ጮኸ፥ ጌታም ሰማው፥ ከመከራውም ሁሉ አዳነው።


ለችግረኛና ለምስኪን የሚያስብ ምስጉን ነው፥ ጌታ በክፉ ቀን ያድነዋል።


ጌታን የምትወዱ፥ ክፋትን ጥሉ፥ እርሱ የቅዱሳኑን ነፍሶች ይጠብቃል፥ ከክፉዎችም እጅ ያድናቸዋል።


ወደ ልቡም ተመልሶ እንዲህ አለ ‘ምግብ የሚተርፋቸው የአባቴ ተቀጣሪዎች ስንት ናቸው? እኔ ግን ከዚህ በራብ እጠፋለሁ።


እነሆም፥ የጌታ መልአክ ቀረበ፤ በቤትም ውስጥ ብርሃን በራ፤ ጴጥሮስንም ጎድኑን መትቶ አነቃውና “ፈጥነህ ተነሣ፤” አለው። ሰንሰለቶቹም ከእጁ ወደቁ።


ሁለት ዓመትም ከሞላ በኋላ ጶርቅዮስ ፊስጦስ በፊልክስ ፈንታ ተተካ። ፊልክስም አይሁድን ደስ ያሰኝ ዘንድ ወዶ ጳውሎስን እንደታሰረ ተወው።


ፊስጦስ ግን አይሁድን ደስ ያሰኝ ዘንድ ወዶ ጳውሎስን “ወደ ኢየሩሳሌም ወጥተህ ስለዚህ ነገር ከዚያው በፊቴ ትፋረድ ዘንድ ትወዳለህን?” ብሎ መለሰለት።


የጌታ መልአክ ግን በሌሊት የወኅኒውን ደጅ ከፍቶ አወጣቸውና


ታዲያ፥ መላእክት ሁሉ መዳንን ስለሚቀበሉ ሰዎች፥ ለአገልግሎት የሚላኩ አገልጋይ መናፍስት አይደሉምን?


እንግዲህ እነሆ፥ ጌታ እግዚአብሔርን የሚያመልኩትን ከፈተና እንዴት እንደሚያድናቸው፥ እንዲሁም በደለኞችን እንዴት በቅጣት ስር ለፍርድ ቀንም ጠብቆ እንደሚያቈያቸው ያውቃል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች