ሐዋርያት ሥራ 11:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)12 መንፈስም ሳልጠራጠር ከእነርሱ ጋር እሄድ ዘንድ ነገረኝ። እነዚህም ስድስቱ ወንድሞች ደግሞ ከእኔ ጋር መጡ፤ ወደዚያ ሰውም ቤት ገባን። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም12 መንፈስ ቅዱስም ምንም ሳላወላውል ከእነርሱ ጋራ እንድሄድ ነገረኝ። እነዚህም ስድስት ወንድሞች ከእኔ ጋራ ሄዱ፤ ወደ ሰውየውም ቤት ገባን። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም12 ያላንዳች ማመንታት ከእነርሱ ጋር እንድሄድም መንፈስ ቅዱስ ነገረኝ፤ እነዚህ ስድስት ወንድሞችም ከእኔ ጋር ነበሩ፤ ከእነርሱም ጋር አብረን ቆርኔሌዎስ ወደ ተባለው ሰው ቤት ገባን። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)12 መንፈስ ቅዱስም፦ ‘ሳትጠራጠር አብረሃቸው ሂድ’ አለኝ፤ እነዚህ ስድስቱ ወንድሞቻችንም ተከትለውኝ መጡና ወደዚያ ሰው ቤት ገባን። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)12 መንፈስም ሳልጠራጠር ከእነርሱ ጋር እሄድ ዘንድ ነገረኝ። እነዚህም ስድስቱ ወንድሞች ደግሞ ከእኔ ጋር መጡ ወደዚያ ሰውም ቤት ገባን። ምዕራፉን ተመልከት |