Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሐዋርያት ሥራ 10:42 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

42 ለሕዝብም እንድንሰብክና በሕያዋንና በሙታን ሊፈርድ በእግዚአብሔር የተወሰነ እርሱ እንደሆነ እንመሰክር ዘንድ አዘዘን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

42 ለሕዝቡ እንድንሰብክና በሕያዋንና በሙታንም ላይ እንዲፈርድ እግዚአብሔር የሾመው እርሱ መሆኑን እንድንመሰክር እርሱ ራሱ አዘዘን፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

42 ይህን ነገር ለሕዝቡ እንድናበሥር እርሱ በሕያዋንና በሙታን ላይ እንዲፈርድ በእግዚአብሔር የተሠየመ መሆኑን እንድንመሰክር አዞናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

42 በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ በሕ​ያ​ዋ​ንና በሙ​ታን ላይ ፈራጅ ሆኖ የተ​ሾመ እርሱ እንደ ሆነ ለሕ​ዝብ እና​ስ​ተ​ምር ዘንድ አዘ​ዘን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

42 ለሕዝብም እንድንሰብክና በሕያዋንና በሙታን ሊፈርድ በእግዚአብሔር የተወሰነ እርሱ እንደ ሆነ እንመሰክር ዘንድ አዘዘን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሐዋርያት ሥራ 10:42
24 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

መልካም ሆነ ወይም ክፉ፥ በሥጋችን እንደ ሠራነው ዋጋችንን ለመቀበል፥ ሁላችን በክርስቶስ የፍርድ ዙፋን ፊት እንቆማለን።


ነገር ግን በሕያዋንና በሙታን ላይ ሊፈርድ ለተዘጋጀው ለእርሱ መልስ ይሰጡበታል።


በእግዚአብሔር ፊት፥ በሕያዋንና በሙታንም ላይ በሚፈርደው በጌታ በክርስቶስ ኢየሱስ ፊት፥ በመገለጡና በመንግሥቱም አጥብቄ አዝዝሃለሁ፤


ቀንቀጥሮአልና፤ በዚያም ቀን ባዘጋጀው ሰው እጅ በዓለሙ ላይ በጽድቅ ሊፈርድ አለው፤ ስለዚህም እርሱን ከሙታን በማስነሣቱ ሁሉን አረጋግጦአል።”


“እነሆ በቶሎ እመጣለሁ፤ ለእያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን እከፍል ዘንድ ዋጋዬ ከእኔ ጋር አለ።


እነሆ ከደመና ጋር ይመጣል፤ ዐይንም ሁሉ የወጉትም ያዩታል፤ የምድርም ወገኖች ሁሉ ስለ እርሱ ዋይ ዋይ ይላሉ። አዎን፤ አሜን።


ከእንግዲህም ወዲህ ጻድቅ ፈራጅ የሆነ ጌታ በዚያ ቀን ሊሸልመኝ የጽድቅ አክሊል አዘጋጅቶ ይጠብቀኛል፤ ደግሞም ለእኔ ብቻ ሳይሆን መገለጡን በፍቅር ለናፈቁት ሁሉ ነው።


“ሂዱና ቆማችሁ የዚህን ሕይወት ቃል ሁሉ ለሕዝብ በመቅደስ ንገሩ፤” አላቸው።


ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኃይልን ትቀበላላችሁ፤ በኢየሩሳሌምም በይሁዳም ሁሉ በሰማርያም እስከ ምድር ዳርም ድረስ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ፤” አለ።


አምስት ወንድሞች አሉኝና፤ እነርሱ ደግሞ ወደዚህ ሥቃይ ስፍራ እንዳይመጡ ይመስክርላቸው’ አለ።


የሰው ልጅስ በተወሰነው መሠረት ይሄዳል፤ ነገር ግን አሳልፎ ለሚሰጠው ሰው ወዮለት።”


እርሱም ስለ ጽድቅና ራስን ስለ መግዛት ስለሚመጣውም ኩነኔ ሲነጋገር ሳለ፥ ፊልክስ ፈርቶ “አሁንስ ሂድ፥ በተመቸኝም ጊዜ ልኬ አስጠራሃለሁ፤” ብሎ መለሰለት።


ይህም እኔ በወንጌል እንዳስተማርሁት በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል እግዚአብሔር የሰዎችን የተሰወሩ ነገሮች በሚፈርድበት ቀን ይሆናል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች