Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ጢሞቴዎስ 3:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 አንተ ግን በተማርህበትና በጽኑ ባመንኸበት ነገር ሳትናወጥ ኑር፤ ከማን እንደ ተማርኸው ታውቃለህና፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 አንተ ግን በተማርኸውና በተረዳኸው ጽና፤ ይህን ከማን እንደ ተማርኸው ታውቃለህና፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 አንተ ግን የተማርከው ከማን እንደ ሆነ ስለምታውቅ በተማርከውና እውነቱን በተረዳኸው ጽና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 አንተ ግን በተማርህበትና በተረዳህበት ነገር ጸንተህ ኑር፤ ከማን እንደ ተማርኸው ታውቃለህና፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 አንተ ግን በተማርህበትና በተረዳህበት ነገር ጸንተህ ኑር፥ ከማን እንደ ተማርኸው ታውቃለህና፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ጢሞቴዎስ 3:14
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ስለዚህም የመልእክትን ቃል፥ እርሱም የእግዚአብሔርን ቃል ከእኛ በተቀበላችሁ ጊዜ፥ በእውነት እንዳለ በእናንተ በአማኞች ደግሞ እንደሚሠራ እንደ እግዚአብሔር ቃል እንጂ እንደ ሰው ቃል አድርጋችሁ ስላልተቀበላችሁት፥ እኛ ደግሞ እግዚአብሔርን ሳናቋርጥ እናመሰግናለን።


በብዙ ምስክሮች ፊት ከእኔ የሰማኸውን ታማኝ ለሆኑ ሌሎችንም ደግሞ ማስተማር ለሚችሉ ሰዎች አደራ ስጥ።


በክርስቶስ ኢየሱስ ባለ እምነትና ፍቅር ከእኔ የሰማኸውን እውነተኛ ቃላት ምሳሌ አድርገህ ያዝ፤


ወንጌላችን በኃይልና በመንፈስ ቅዱስ፥ በብዙም መረዳት እንጂ በቃል ብቻ ወደ እናንተ አልመጣምና፤ ስለ እናንተ ስንል በእናንተ መካከል ምን ዓይነት ሰዎች እንደ ነበርን እናንተው ታውቃላችሁ።


ከክፉ ኅሊና ለመንጻት ልባችንን ተረጭተንና ሰውነታችንን በንጹህ ውሃ ታጥበን፥ በቅን ልብ በፍጹም እምነት እንቅረብ፤


እናንተም ሁላችሁ በተስፋ የምትጠባበቁትን ነገር እስክትጨብጡ ድረስ ትጋታችሁን እስከ መጨረሻ እንድታሳዩ እንመኛለን፤


ለራስህና ለምታስተምረው ትምህርት ተጠንቀቅ፤ በእነዚህም ነገሮች ጽና፤ ይህን ብታደርግ፥ ራስህንና የሚሰሙህን ታድናለህ።


እንዲሁም ከሕፃንነትህ አንሥቶ በክርስቶስ ኢየሱስ በማመን ወደሚገኘው መዳን የሚመራህን ጥበብ ሊሰጡህ የሚያስችሉትን ቅዱስ መጻሕፍትን አውቀሃልና።


ይህ ሰው አንድ ቀን ከሌላ ቀን እንደሚሻል ያስባል፤ ሌላው ግን ቀን ሁሉ አንድ እንደሆነ ያስባል፤ እያንዳንዱ በገዛ አእምሮው አጥብቆ ይረዳ።


እንዲህም የምጋደለው ልባቸው እንዲጽናና፥ በፍቅርም በአንድነት እንዲተሳሰሩ፥ በፍጹም ማስተዋልም የሚገኘውን ባለጠግነት ሁሉ እንዲኖራቸው፥ የእግዚአብሔርንም ምሥጢር እርሱንም ክርስቶስን እንዲያውቁ ነው፤


ቀንቀጥሮአልና፤ በዚያም ቀን ባዘጋጀው ሰው እጅ በዓለሙ ላይ በጽድቅ ሊፈርድ አለው፤ ስለዚህም እርሱን ከሙታን በማስነሣቱ ሁሉን አረጋግጦአል።”


እውነተኛውንም ትምህርት ለመምከርና ተቃዋሚዎቹን ለመገሠጽ እንዲችል፥ እንደተማረው በታመነ ቃል ይጽና።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች