Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 9:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 የሳኦል ልጅ፥ የዮናታን ልጅ መፊቦሼት ወደ ዳዊት በመጣ ጊዜ፥ በግምባሩም ወድቆ እጅ ነሣ። ዳዊትም፥ “መፊቦሼት!” ብሎ ጠራው። እርሱም፥ “እነሆ፤ አገልጋይህ” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 የሳኦል ልጅ፣ የዮናታን ልጅ ሜምፊቦስቴ ወደ ዳዊት በመጣ ጊዜ፣ አክብሮቱን ለመግለጥ ለጥ ብሎ እጅ ነሣ። ዳዊትም፣ “ሜምፊቦስቴ” ብሎ ጠራው። እርሱም፣ “እነሆ፤ አገልጋይህ” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 የሳኦል የልጅ ልጅ፥ የዮናታን ልጅ መፊቦሼት በመጣ ጊዜ በዳዊት ፊት ወደ መሬት ለጥ ብሎ እጅ በመንሣት አክብሮቱን ገለጠ። ዳዊትም “መፊቦሼት!” ሲል ጠራው። መፊቦሼትም “ጌታ ሆይ! እነሆ አገልጋይህ ነኝ!” ሲል መለሰ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 የሳ​ኦ​ልም ልጅ የዮ​ና​ታን ልጅ ሜም​ፌ​ቡ​ስቴ ወደ ዳዊት መጣ፤ በግ​ን​ባ​ሩም ወድቆ ሰገ​ደ​ለት፤ ንጉሥ ዳዊ​ትም፥ “ሜም​ፌ​ቡ​ስቴ ሆይ፥” አለ፤ እር​ሱም፥ “እነ​ሆኝ አገ​ል​ጋ​ይህ” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 የሳኦልም ልጅ የዮናታን ልጅ ሜምፊቦስቴ ወደ ዳዊት መጣ፥ በግምባሩም ወድቆ እጅ ነሣ፥ ዳዊትም፦ ሜምፊቦስቴ ሆይ፥ አለ፥ እርሱም፦ እነሆኝ ባሪያህ አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 9:6
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የዮናታንም ልጅ መሪበ-ኣል ነበረ፤ መሪበ-ኣልም ሚካን ወለደ።


የዮናታንም ልጅ መሪ-በኣል ነበረ፤ መሪ-በኣልም ሚካን ወለደ።


ከዚያም ንጉሡ ጺባን፥ “የመፊቦሼት የነበረው ሁሉ ከእንግዲህ ያንተ ነው” አለው። ጺባም፥ “እጅ እነሣለሁ፤ ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፤ በፊትህ ሞገስ ላግኝ” አለው።


አቢግያም ዳዊትን ባየች ጊዜ ወዲያው ከአህያዋ ወርዳ፥ በዳዊትም ፊት በግምባርዋ ተደፍታ እጅ ነሣች።


ልጁ ከሄደ በኋላ፥ ዳዊት ከድንጋዩ በስተ ደቡብ ከተደበቀበት ቦታ ወጥቶ በዮናታን ፊት ሦስት ጊዜ በምድር ላይ ተደፍቶ ሰገደለት፤ ከዚያም ተሳሳሙ፤ ተላቀሱም፤ በይበልጥ ያለቀሰው ግን ዳዊት ነበር።


እርሱም ከፊታቸው ቀደመ፥ ወደ ወንድሙም እስኪደርስ ድረስ ወደ ምድር ሰባት ጊዜ ሰገደ።


ዓይኑንም አነሣና እነሆ፥ ሦስት ሰዎች በፊቱ ቆመው አየ፥ ባያቸውም ጊዜ ሊቀበላቸው ከድንኳኑ ደጃፍ ተነሥቶ ሮጠ፥ ወደ ምድርም ሰገደ፥ እንዲህም አለ፦


የሳኦል ልጅ ዮናታን ሁለት እግሮቹ ሽባ የሆኑ አንድ ልጅ ነበረው። እርሱም የሳኦልና የዮናታን አሟሟት ወሬ ከኢይዝራኤል በመጣ ጊዜ የአምስት ዓመት ልጅ ነበረ። ሽባ የሆነውንም በዚህ ጊዜ ሞግዚቱ አንሥታው በጥድፊያ ስትሸሽ በመውደቁ ነው። ስሙም መፊቦሼት ይባል ነበር።


ስለዚህም ንጉሥ ዳዊት፥ መፊቦሼትን ከዓሚኤል ከማኪር ቤት ከሎደባር ልኮ አስመጣው።


ወደ ኋላውም ዞር ሲል አየኝና ጠራኝ፤ እኔም፥ ‘እነሆ አለሁ!’ አልኩት።


ንጉሥ ዳዊት በራሱና በሳኦል ልጅ በዮናታን መካከል በጌታ ፊት ስላደረጉት መሐላ ሲል የሳኦልን ልጅ፥ የዮናታንን ልጅ መፊቦሼትን ከሞት አተረፈ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች