2 ሳሙኤል 5:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)6 ንጉሡና ሰዎቹ በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን ኢያቡሳውያንን ለመውጋት ወደዚያ ዘመቱ። እነርሱም፥ “ዳዊት እዚህ ሊገባ አይችልም” ብለው ስላሰቡ ዳዊትን፥ “ዕውሮችና አንካሶች እንኳ ስለሚከላከሉህ ወደዚህች አትገባም” አሉት። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም6 ንጉሡና ሰዎቹ በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን ኢያቡሳውያንን ለመውጋት ወደዚያ ሄዱ። ኢያቡሳውያንም፣ “ዳዊት እዚህ ሊገባ አይችልም” ብለው ስላሰቡ ዳዊትን፣ “ዕውሮችና ዐንካሶች እንኳ ይከለክሉሃልና ወደዚህች አትገባም” አሉት። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም6 ንጉሡና ሰዎቹ ከኢያቡሳውያን ጋር ለመዋጋት በኢየሩሳሌም ላይ ዘመቱ፤ ዳዊት ወደዚያ የማይገባ መስሎአቸው የምድሪቱ ነዋሪዎች ዳዊትን “አንተ ወደዚህ ልትገባ አትችልም፤ ዕውሮችና አንካሶች እንኳ ይመልሱሃል” አሉት። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)6 ዳዊትና ሰዎቹም በሀገሩ ውስጥ ወደሚኖሩት ወደ ኢያቡሴዎናውያን ወደ ኢየሩሳሌም ሄዱ፤ እነርሱም ዳዊትን፥ “ወደዚህ አትገባም” አሉት። ዕውሮችና አንካሶችም ወደዚህ አትገባም ብለው ተቃወሙት። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)6 ንጉሡና ሰዎቹም በአገሩ ውስጥ ከተቀመጡት ከኢያቡሳውያን ጋር ለመዋጋት ወደ ኢየሩሳሌም ሄዱ፥ እነርሱም፦ ዳዊት ወደዚህ ሊገባ አይችልም ብለው አስበው ነበርና ዳዊትን፦ ዕውሮችንና አንካሶችን ካላወጣህ በቀር ወደዚህ አትገባም አሉት። ምዕራፉን ተመልከት |