2 ሳሙኤል 3:39 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)39 ምንም እንኳ ዛሬ የተቀባሁ ንጉሥ ብሆንም፥ እኔ ደካማ ሰው ነኝ፤ እነዚህ የጽሩያ ልጆች እጅግ በርትተውብኛል። ጌታ ለክፉ አድራጊ የእጁን ይስጠው።” ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም39 ምንም እንኳ ዛሬ የተቀባሁ ንጉሥ ብሆንም፣ እኔ ደካማ ሰው ነኝ፤ እነዚህ የጽሩያ ልጆች እጅግ በርትተውብኛል። እግዚአብሔር ለክፉ አድራጊ የእጁን ይስጠው።” ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም39 ምንም እንኳ እኔ እግዚአብሔር መርጦ የሾመኝ ንጉሥ ብሆን ዛሬ ደካማነት ተሰምቶኛል፤ እነዚህ የጸሩያ ልጆች በእኔ ላይ እጅግ የበረቱ ዐመፀኞች ሆነውብኛል፤ እነዚህን ነፍሰ ገዳዮች እግዚአብሔር ራሱ የሚገባቸውን ቅጣት ይስጣቸው!” ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)39 እኔም ዛሬ ዘመዱ እንደ ሆንሁ፥ እርሱም በንጉሡ ዘንድ የተሾመ እንደ ሆነ አታውቁምን? እነዚህም ሰዎች የሦርህያ ልጆች በርትተውብኛል፤ እግዚአብሔርም ክፋት በሠራ ላይ እንደ ክፋቱ ይመልስበት” አላቸው። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)39 እኔም ዛሬ ምንም ለመንገሥ የተቀባሁ ብሆን ደካማ ነኝ፥ እነዚህም ሰዎች የጽሩያም ልጆች በርትተውብኛል፥ እግዚአብሔር ክፋት በሠራ ላይ እንደ ክፋቱ ይመልስበት አላቸው። ምዕራፉን ተመልከት |