Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 23:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ነገር ግን ክፉ ሰዎች ሁሉ፥ በእጅ እንደማይሰበሰብ እንደ እሾኽ ይጣላሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ነገር ግን ምናምንቴ ሰዎች ሁሉ፣ በእጅ እንደማይሰበሰብ እንደ እሾኽ ይጣላሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ክፉዎች ግን እንደ ተጣለ እሾኽ ስለ ሆኑ ማንም በእጁ ሊዳስሳቸው አይችልም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 እነ​ዚህ ሁሉ ግን ሰው በእጁ እን​ደ​ማ​ይ​ዘው፥ እንደ ተጣለ እሾህ ናቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ዓመፀኞች ሁሉ ግን ሰው በእጁ እንደማይዘው፥ እንደ ተጣለ እሾህ ናቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 23:6
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አንተም የሰው ልጅ ሆይ፥ ኩርንችትና እሾህ ከአንተ ጋር ቢኖሩም፥ በጊንጦች መካከል ብትቀመጥም፥ አትፍራ፥ ቃላቸውንም አትፍራ፥ እነርሱ ዓመፀኛ ቤት ናቸውና ቃላቸውን አትፍራ፥ ፊታቸውንም አትፍራው።


አሕዛብም እንደ ተቃጠለ ኖራ፥ ተቆርጦም በእሳት እንደ ተቃጠለ እሾህ ይሆናሉ።”


በእሾህ መካከል እንዳለ የሱፍ አበባ፥ እንዲሁ ወዳጄ በልጃገረዶች መካከል ናት።


በዚህ ጊዜ የቢክሪ ልጅ ስሙ ሼባዕ የተባለ አንድ ከንቱ ብንያማዊ በዚያ ነበረ፤ እርሱም መለከት ነፍቶ እንዲህ ሲል ጮኸ፤ “እኛ ከዳዊት ድርሻ የለንም፤ ከእሴይም ልጅ ርስት የለንም፤ እስራኤል ሆይ፤ እያንዳንድህ ወደ ድንኳንህ ተመለስ!”


የዔሊም ልጆች ለጌታ ክብር የማይሰጡ ስድ አደጎች ነበሩ።


ክፉ ሰዎች ከመካከላችሁ ተነሥተው አንተ የማታውቃቸውን፥ ‘ሌሎች አማልክትን ሄደን እናምልክ’ በማለት የከተማቸውን ሕዝብ እያሳቱ ቢሆን፥


“እሾህንና አሜከላን ታበቅልብሃለች፥ የምድርንም ቡቃያ ትበላለህ።”


የሰው ልጅ መላእክቱን ይልካል፤ ከመንግሥቱም እንቅፋቶችን ሁሉና ዓመፃን ይሰበስባሉ፤


እሾህና ኩርንችት ቢያበቅልብኝ፥ እኔ አልቈጣም፥ በእነርሱ ላይ ተራምጄ አቃጥላቸዋለሁ።


እንደ ተጠላለፈ እሾህ፥ በመጠጣቸውም እንደሰከሩ ቢሆኑ እንኳ እንደ ደረቅ ገለባ ፈጽመው ይጠፋሉ።


አሁንም በጌታችንና በመላው ቤተሰቡ ላይ መከራ እያንዣበበ ስለሆነ፥ ምን እንደምታደርጊ አስቢበት፤ እርሱ እንደሆነ እንዲህ ያለ ባለጌ ሰው ስለሆነ፥ ማንም ደፍሮ የሚነግረው የለም።”


ከእነርሱ የተሻለ የተባለው እንደ አሜከላ ነው፥ ቅን የተባለው እንደ ኩርንችት ነው፤ ጠባቂዎችህ የሚጐበኙበት ቀን መጥቷል፤ መሸበራቸውም አሁን ይሆናል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች