2 ሳሙኤል 20:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)10 አማሳይ ግን በኢዮአብ እጅ ሰይፍ መኖሩን ልብ ስላላለ ጥንቃቄ አላደረገም፤ ስለዚህ ኢዮአብ ሰይፉን ሆዱ ላይ ሻጠበት፤ አንጀቱም መሬት ላይ ተዘረገፈ፤ መድገምም አላስፈለገውም፥ አማሳይ በዚያው ሞተ። ከዚህ በኋላ ኢዮአብና ወንድሙ አቢሳ፥ የቢክሪን ልጅ ሼባዕን ማሳደድ ጀመሩ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም10 አሜሳይ ግን በኢዮአብ እጅ ሰይፍ መኖሩን ልብ ስላላለ ጥንቃቄ አላደረገም፤ ስለዚህ ኢዮአብ ሰይፉን ሆዱ ላይ ሻጠበት፤ አንጀቱም መሬት ላይ ተዘረገፈ፤ ከዚያም ኢዮአብ መድገም ሳያስፈልገው፣ አሜሳይ በዚያው ሞተ። ከዚህ በኋላ ኢዮአብና ወንድሙ አቢሳ፣ የቢክሪን ልጅ ሳቤዔን ማሳደድ ጀመሩ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም10 ኢዮአብ በሌላው እጁ የያዘውን ሰይፍ ስላላየ ዐማሣ አልተጠነቀቀም ነበርና ኢዮአብ በሆዱ ሻጠበት፤ የሆድ ዕቃውም መሬት ላይ ተዘረገፈ፤ ወዲያውኑ ስለ ሞተም ኢዮአብ በድጋሚ አልወጋውም። ከዚህ በኋላ ኢዮአብና ወንድሙ አቢሳ የቢክሪን ልጅ ሼባዕን ማሳደዳቸውን ቀጠሉ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)10 አሜሳይ ግን በኢዮአብ እጅ ከነበረው ሰይፍ አልተጠነቀቀም ነበር፤ ኢዮአብም ሆዱን ወጋው፤ አንጀቱንም በምድር ላይ ዘረገፈው፤ ሁለተኛም አልወጋውም፤ ሞተም። ኢዮአብና ወንድሙ አቢሳም የቢኮሪን ልጅ ሳቡሄን አሳደዱ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)10 አሜሳይ ግን በኢዮአብ እጅ ከነበረው ሰይፍ አልተጠነቀቀም ነበር፥ ኢዮአብም ሆዱን ወጋው፥ አንጀቱንም በምድር ላይ ዘረገፈው፥ ሁለተኛም አልወጋውም፥ ሞተም። ምዕራፉን ተመልከት |