Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 19:33 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

33 ባርዚላይ በዕድሜ የገፋ የሰማንያ ዓመት ሽማግሌ ነበር፤ እጅግ ባለጸጋ ስለ ነበረም ንጉሡ በማሕናይም ሳለ የሚመገበውን አምጥቶለት ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

33 ንጉሡም ቤርዜሊን፣ “ከእኔ ጋራ ተሻገርና በኢየሩሳሌም ዐብረኸኝ ኑር፤ እኔ እመግብሃለሁ” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

33 ንጉሡም ባርዚላይ “ከእኔ ጋር ወደ ኢየሩሳሌም ና፤ እኔም በተድላና በደስታ እንድትኖር አደርግሃለሁ” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

33 ንጉ​ሡም ቤር​ዜ​ሊን፥ “አንተ ከእኔ ጋር ዮር​ዳ​ኖ​ስን ትሻ​ገ​ራ​ለህ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ያረጀ ሰው​ነ​ት​ህን ከእኔ ጋር እጦ​ረ​ዋ​ለሁ” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

33 ንጉሡም ቤርዜሊን፦ በኢየሩሳሌም እቀልብህ ዘንድ ከእኔ ጋር እለፍ አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 19:33
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዳዊት ማሕናይም ሲደርስ፥ ከአሞናውያን ከተማ ከራባ የመጣው፥ የናዖስ ልጅ ሾቢ፥ ከሎዶባር የመጣው የዓሚኤል ልጅ ማኪርና ከሮግሊም የመጣው ገለዓዳዊው ቤርዜሊ


እንዲሁም ገለዓዳዊው ባርዚላይ ከሮገሊም ወረደ፤ ንጉሡን ለመሸኘትም አብሮት ዮርዳኖስን ተሻገረ።


ንጉሡም ባርዚላይ፥ “ከእኔ ጋር ተሻገርና በኢየሩሳሌም አብረኸኝ ኑር፤ የሚያስፈልግህን እኔ አደርግልሃለሁ” አለው።


ከዚያም ጺባ ንጉሡን፥ “ጌታዬ ንጉሥ፥ አገልጋዩን ያዘዘውን ሁሉ፥ አገልጋይህ ይፈጽመዋል” አለው። ስለዚህም መፊቦሼት እንደ አንዱ ሆኖ ከዳዊት ማእድ ይበላ ነበር።


እንዲሁም እርሱ ጌታ ኢየሱስ ከኃያላን መላእክቱ ጋር ከሰማይ በእሳት ነበልባል በሚመጣበት ጊዜ መከራን ለተቀበላችሁት ከእኛ ጋር ዕረፍትን ይሰጣችኋል፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች