Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 18:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 አቤሴሎምን ጫካ ወስደው በትልቅ ጉድጓድ ውስጥ ጣሉት፤ በላዩም ትልልቅ ድንጋይ ከመሩበት። እስራኤልም ሁሉ ወደየቤታቸው ሸሹ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 አቤሴሎምን ጫካ ወስደው በትልቅ ጕድጓድ ውስጥ ወርውረው ጣሉት፤ በላዩም ትልልቅ ድንጋይ ከመሩበት። በዚህ ጊዜ እስራኤላውያን ሁሉ ወደ የቤታቸው ሸሹ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 የአቤሴሎምንም ሬሳ ወስደው በደን ውስጥ በሚገኘው ጥልቅ ጒድጓድ ውስጥ ጣሉት፤ በእርሱም ላይ ብዙ ትልልቅ ድንጋይ ከምረው እንዲሸፈን አደረጉት፤ እስራኤላውያንም ሁሉ ሸሽተው እያንዳንዱ ሰው ወደየቤቱ ገባ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 አቤ​ሴ​ሎ​ም​ንም ወስዶ በበ​ረሓ ባለ በታ​ላቅ ገደል ውስጥ ጣለው፤ እጅ​ግም ታላቅ የሆነ የድ​ን​ጋይ ክምር ከመ​ረ​በት፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ሸሽ​ተው ወደ ድን​ኳ​ና​ቸው ገቡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 አቤሴሎምንም ወስደው በዱር ባለ በታላቅ ጕድጓድ ውስጥ ጣሉት፥ እጅግም ታላቅ የሆነ የድንጋይ ክምር ከመሩበት፥ እስራኤልም ሁሉ እያንዳንዱ ወደ ድንኳኑ ሸሸ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 18:17
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የጋይንም ንጉሥ እስከ ማታ ድረስ በዛፍ ላይ ሰቀለው፤ ፀሐይም በገባች ጊዜ ኢያሱ አዘዘ፥ ሬሳውንም ከዛፍ አወረዱት፥ በከተማይቱም በር አደባባይ ጣሉት፥ በእርሱም ላይ እስከ ዛሬ ድረስ ያለውን ታላቅ የድንጋይ ክምር ከመሩበት።


በእርሱም ላይ እስከ ዛሬ ድረስ ያለ ታላቅ የድንጋይ ክምር ከመሩ፤ ጌታም ከጽኑ ቁጣው ተመለሰ። ስለዚህም የዚያ ስፍራ ስም እስከ ዛሬ ድረስ የአኮር ሸለቆ ተብሎ ተጠራ።


የጻድቅ መታሰቢያ ለበረከት ነው፥ የክፉ ስም ግን ይጠፋል።


ከዚህም በኋላ ሴቲቱ ብልኅ ምክሯን ይዛ ወደ ሕዝቡ ሁሉ ሄደች፤ እነርሱም የቢክሪን ልጅ የሼባዕን ራስ ቆርጠው ለኢዮአብ ወረወሩለት፤ ስለዚህ ኢዮአብ መለከቱን ነፋ፤ ሰዎቹም ከከተማዪቱ ርቀው በየአቅጣጫው ተበታተኑ፤ እያንዳንዳቸውም ወደየቤታቸው ሄዱ፤ ኢዮአብም ወደ ንጉሡ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ።


በዚህ ጊዜ የቢክሪ ልጅ ስሙ ሼባዕ የተባለ አንድ ከንቱ ብንያማዊ በዚያ ነበረ፤ እርሱም መለከት ነፍቶ እንዲህ ሲል ጮኸ፤ “እኛ ከዳዊት ድርሻ የለንም፤ ከእሴይም ልጅ ርስት የለንም፤ እስራኤል ሆይ፤ እያንዳንድህ ወደ ድንኳንህ ተመለስ!”


በል አሁን ተነሥተህ ውጣና አገልጋዮችህን አበረታታ፤ ባትወጣ ግን በዚች ሌሊት አንድም ሰው አብሮህ እንደማይሆን በጌታ ስም እምላለሁ፤ ይህ ደግሞ ከልጅነትህ ጀምሮ እስካሁን ድረስ ከደረሰብህ ክፉ ነገር ሁሉ የባሰ መከራ ያሰከትልብሃል።”


ፀሐይም ልትገባ በቀረበች ጊዜ ኢያሱ አዘዘ፥ ከዛፎችም አወረዱአቸው፥ ተሸሽገውም በነበሩበት ዋሻ ጣሉአቸው፥ እስከ ዛሬም ድረስ በዋሻው አፍ ታላላቅ ድንጋይ ተደርጎአል።


‘ይህ ልጃችን እልከኛና ዓመፀኛ ነው፤ አይታዘዘንም፤ አባካኝና ሰካራም ነው’ ብለው ለአለቆች ይንገሯቸው።


ከዚያም በኋላ የከተማዪቱ ሰዎች ሁሉ እስኪሞት ድረስ በድንጋይ ይውገሩት፤ ክፉውንም ከመካከልህ አስወግድ፤ እስራኤልም ሁሉ ይህን ሰምቶ ይፈራል።


ፍልስጥኤማውያንም ተዋጉ፤ እስራኤላውያንም ስለ ተሸነፉ እያንዳንዱ ወደየድንኳኑ ሸሸ። ታላቅ እልቂትም ሆነ፤ ከእስራኤልም ሠላሳ ሺህ እግረኛ ወታድሮች ወደቁ።


ስለዚህም ኢዮራም ሠረገሎቹን በመላ አሰልፎ ወደ ጻዒር ዘመተ፤ የኤዶም ሠራዊትም ከበባቸው፤ በሌሊትም እርሱና የሠረገላዎቹ አዛዦች ከበባውን ጥሰው ሲያመልጡ፥ ወታደሮቹ ወደየቤታቸው ተበታተኑ፤


ይሁዳም ድል ተመታ፤ ወታደሮቹም ሁሉ ተበታትነው ወደየቤታቸው ተመለሱ።


ንጉሡ ፊቱን ሸፍኖ፥ “ልጄ አቤሴሎም ሆይ፥ ልጄ አቤሴሎም፥ ልጄ ሆይ፥ ልጄን! ልጄን!” እያለ በታላቅ ድምፅ ጮኸ።


ስለዚህ ንጉሡ ተነሥቶ በበሩ አጠገብ ተቀመጠ፤ ለሕዝቡም፥ “እነሆ ንጉሡ በበሩ አጠገብ ተቀምጦአል” ተብሎ በተነገረ ጊዜ ሕዝቡ በሙሉ ወደ ንጉሡ መጣ። በዚያን ጊዜ እስራኤላውያን በሙሉ ወደየቤታቸው ሸሽተው ነበር።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች