2 ሳሙኤል 14:32 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)32 አቤሴሎምም፥ ኢዮአብን፥ “‘ከገሹር ለምን መጣሁ? ለእኔ እስካሁንም እዚያው ብሆን ይሻለኝ ነበር ብሏል፥’ ብለህ እንድትነግርልኝ ወደ ንጉሡ ልልክህ ወደ እኔ ና ብዬ አስጠራሁህ፤ አሁንም ቢሆን ወደ ንጉሡ ፊት መቅረብ እፈልጋለሁ፤ ምንም ዓይነት በደል ከተገኘብኝ ይግደለኝ” አለው። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም32 አቤሴሎምም፣ ኢዮአብን፣ “ከጌሹር ለምን መጣሁ? ‘ለእኔ እስካሁንም እዚያው ብሆን ይሻለኝ ነበር ብሏል ብለህ እንድትነግርልኝ ወደ ንጉሡ እልክህ ዘንድ ወደ እኔ ና’ ብዬ አስጠራሁህ፤ አሁንም ቢሆን፤ የንጉሡን ዐይን ማየት እፈልጋለሁ፤ ምንም ዐይነት በደል ከተገኘብኝ ይግደለኝ” አለው። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም32 አቤሴሎምም “አንተ እኔ ስጠራህ ስላልመጣህ ነው፤ ወደ ንጉሡ ሄደህ ‘ከገሹር ወጥቼ ወደዚህ ለምን መጣሁ? እዚያው ቈይቼ ብሆን ኖሮ በተሻለኝ ነበር’ ብለህ ስለ እኔ ሁኔታ ጠይቅልኝ፤ እንዲሁም ከንጉሡ ጋር መገናኘት እችል ዘንድ ሁኔታዎችን አመቻችልኝ፤ እኔ በደለኛ ሆኜ ከተገኘሁ ሞት ይፍረድብኝ” አለው። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)32 አቤሴሎምም ኢዮአብን፥ “ከጌድሶር ለምን መጣሁ? በዚያም ተቀምጬ ቢሆን ይሻለኝ ነበር ብለህ እንድትነግረው ወደ ንጉሥ እልክህ ዘንድ ወደ እኔ ና ብዬ ወደ አንተ ላክሁ፤ አሁንም የንጉሡን ፊት አላየሁም፤ ኀጢአት ቢኖርብኝ ይግደለኝ” አለው። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)32 አቤሴሎምም ኢዮአብን መልሶ፦ ከጌሹር ለምን መጣሁ? በዚያም ተቀምጩ ብሆን ይሻለኝ ነበር ብለህ እንድትነግረው ወደ ንጉሡ እልክህ ዘንድ ወደ እኔ ጠራሁህ፥ አሁንም የንጉሡን ፊት ልይ፥ ኃጢአት ቢሆንብኝ ይግደለኝ አለው። ምዕራፉን ተመልከት |