2 ሳሙኤል 13:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)6 ስለዚህ አምኖን የታመመ ሰው መስሎ ተኛ፤ ንጉሡም ሊጠይቀው መጣ፤ አምኖንም፥ “እኅቴ ትዕማር መጥታ፥ እያየሁ ሁለት እንጀራ ጋግራ በእጇ እንድታጐርሰኝ እለምንሃለሁ” ብሎ ጠየቀው። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም6 ስለዚህ አምኖን የታመመ ሰው መስሎ ተኛ፤ ንጉሡም ሊጠይቀው መጣ፤ አምኖንም፣ “እኅቴ ትዕማር መጥታ፣ እያየሁ ሁለት እንጀራ ጋግራ በእጇ እንድታጐርሰኝ እለምንሃለሁ” ብሎ ጠየቀው። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም6 ስለዚህም አምኖን የታመመ በመምሰል በአልጋው ላይ ተኛ። ንጉሥ ዳዊትም ሊጠይቀው ወደ እርሱ በሄደ ጊዜ አምኖን “እኅቴ ትዕማር እዚህ በአጠገቤ እያየኋት ሁለት እንጀራ ጋግራ እርስዋ ራስዋ እንድታቀርብልኝ ፍቀድላት” አለው። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)6 እንዲሁም አምኖን፥ ታምሜአለሁ ብሎ ተኛ፤ ንጉሡም ሊያየው መጣ፤ አምኖንም ንጉሡን፥ “እኅቴ ትዕማር እንድትመጣና እኔ እያየሁ ሁለት እንጎቻ እንድታበስልልኝ፥ ከእጅዋም እንድበላ እለምንሃለሁ” አለው። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)6 እንዲሁም አምኖን፦ ታምሜአለሁ ብሎ ተኛ፥ ንጉሡም ሊያየው በመጣ ጊዜ አምኖን ንጉሡን፦ እኅቴ ትዕማር እንድትመጣና እኔ እያየሁ ሁለት እንጎቻ እንድታደርግልኝ፥ ከእጅዋም እንድበላ እለምንሃለሁ አለው። ምዕራፉን ተመልከት |