Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 13:39 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

39 ንጉሥ ዳዊትም በልጁ ሞት ከደረሰበት ኀዘን ተጽናና፤ ከዚያም መንፈሱ ወደ አቤሴሎም ለመሄድ ናፈቀ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

39 ንጉሥ ዳዊት በልጁ በአምኖን ሞት ከደረሰበት ሐዘን ከተጽናና በኋላ፣ ወደ አቤሴሎም ለመሄድ መንፈሱ ተነሣሣ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

39 ነገር ግን ስለ አምኖን ሞት የነበረበት ሐዘን እየተረሳ በሄደ ቊጥር ልጁን አቤሴሎምን መናፈቅ ጀመረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

39 ንጉ​ሡም ዳዊት አቤ​ሴ​ሎ​ምን መከ​ታ​ተ​ልን ተወ፤ ስለ ሞተው ልጁ ስለ አም​ኖን ተጽ​ና​ንቶ ነበ​ርና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

39 ንጉሡም ዳዊት ስለ አምኖን ሞት ተጽናንቶ ወደ አቤሴሎም ይሄድ ዘንድ እጅግ ናፈቀ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 13:39
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ይስሐቅም ወደ እናቱ ወደ ሣራ ድንኳን አገባት፥ ርብቃንም ወሰዳት፥ ሚስትም ሆነችው፥ ወደዳትም፥ ይስሐቅም ከእናቱ ሞት ተጽናና።


ከብዙ ጊዜ በኋላ የሹዓ ልጅ፥ የይሁዳ ሚስት ሞተች። ይሁዳ ከሐዘኑ ከተጽናና በኋላ ከዓዶላማዊው ከሒራ ጋር የበጎቹን ጠጉር የሚሸልቱ ሰዎች ወዳሉበት ወደ ተምና ሄደ።


ወንዶች ልጆቹና ሴቶች ልጆቹም ሁሉ ሊያጽናኑት ተነሡ፥ መጽናናትን እንቢ አለ፥ እንዲህም አለ፦ “ወደ ልጄ ወደ ሙታን ስፍራ እያዘንሁ እወርዳለሁ።” አባቱም እንደዚህ ስለ እርሱ አለቀሰ።


ሁላችሁን ይናፍቃልና፤ እንደ ታመመም ስለ ሰማችሁ ይተክዛል።


ፍርዶችህን ሁልጊዜ በመፈለግ ነፍሴ በናፍቆት ደቀቀች።


የሠራዊት አምላክ ሆይ፥ ማደሪያዎችህ እንደምን የተወደዱ ናቸው!


ወንዶችና ሴቶች ልጆችህ ለሌላ ሕዝብ ይሰጣሉ፤ ነገር ግን ምንም ለማድረግ አትችልም፤ ከዛሬ ነገ ይመጣሉ በማለትም ዐይኖችህ ሁልጊዜ እነርሱን በመጠባበቅ ይደክማሉ።


አሁንም የአባትህን ቤት እጅጉን ናፍቆሃልና ሂድ፥ ነገር ግን አምላኮቼን ለምን ሰረቅህ?”


የንጉሡ ልብ አቤሴሎምን እንደናፈቀ የጽሩያ ልጅ ኢዮአብ ተረዳ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች