Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 13:29 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 የአቤሴሎምም አገልጋዮች በአምኖን ላይ አቤሴሎም ያዘዛቸውን ፈጸሙ። ከዚያም የንጉሡ ልጆች በሙሉ ተነሥተው በየበቅሎዎቻቸው ላይ ተቀምጠው ሸሹ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 የአቤሴሎምም አገልጋዮች ጌታቸው ያዘዛቸውን በአምኖን ላይ ፈጸሙ። ከዚያም የንጉሡ ልጆች በሙሉ ተነሥተው በየበቅሎዎቻቸው ላይ ተቀምጠው ሸሹ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 ስለዚህ አገልጋዮቹ አቤሴሎም በነገራቸው መመሪያ መሠረት አምኖንን ገደሉ፤ የቀሩትም የዳዊት ወንዶች ልጆች በበቅሎዎቻቸው ተቀምጠው እየጋለቡ ሸሹ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 የአ​ቤ​ሴ​ሎ​ምም አገ​ል​ጋ​ዮች አቤ​ሴ​ሎም እን​ዳ​ዘ​ዛ​ቸው በአ​ም​ኖን ላይ አደ​ረ​ጉ​በት። የን​ጉ​ሡም ልጆች ሁሉ ተነ​ሥ​ተው በየ​በ​ቅ​ሎ​ዎ​ቻ​ቸው ተቀ​ም​ጠው ሸሹ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29 የአቤሴሎምም አገልጋዮች አቤሴሎም እንዳዘዛቸው በአምኖን ላይ አደረጉበት። የንጉሡም ልጆች ሁሉ ተነሥተው በየበቅሎቻቸው ተቀምጠው ሸሹ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 13:29
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የፅብዖን ልጆችም፦ አያና ዓና ናቸው። ይህ ዓና የአባቱን የፅብዖንን አህዮች ሲጠብቅ በበረሓ ውስጥ የፍል ውሃ ምንጮችን ያገኘ ነው።


ስለዚህ እኔን አቃለኸኛል፤ ሚስት እንድትሆንህም የሒታዊውን የኦርዮን ሚስት ወስደሃታልና፥ ሰይፍ ለዘለዓለም ከቤትህ አይርቅም።’ ”


እነርሱ በመንገድ ላይ ሳሉም፥ “አቤሴሎም የንጉሡን ልጆች በሙሉ ፈጃቸው፤ አንድም የተረፈ የለም” የሚል ወሬ ለዳዊት ደረሰው።


እኔ አገልጋይህ ሁለት ወንዶች ልጆች ነበሩኝ፤ ሜዳ ላይ እርስ በርሳቸው ተጣሉ፤ ገላጋይም ስላልነበረ፥ አንዱ ሌላውን መትቶ ገደለው።


በዚህ ጊዜ አቤሴሎም ከዳዊት ሰዎች ጋር ድንገት ተገናኘ፤ አቤሴሎም በበቅሎ ተቀምጦ ይሄድ ስለ ነበር፥ በቅሎዋ ጥቅጥቅ ያለ ቅርንጫፍ ባለው ትልቅ ባሉጥ ሥር በምታልፍበት ጊዜ፥ የአቤሴሎም ራስ በባሉጡ ቅርንጫፍ ተያዘ፤ የተቀመጠበትም በቅሎ በሥሩ ስታልፍ፥ እርሱ በሰማይና በምድር መካከል ተንጠልጥሎ ቀረ።


ንጉሡም አላቸው፦ “የጌታችሁን ባርያዎች ይዛችሁ ሂዱ፥ ልጄንም ሰሎሞንን በበቅሎዬ ላይ አስቀምጡት፥ ወደ ግዮንም አውርዱት፥


ካህኑም ሳዶቅና ነቢዩ ናታን የዮዳሄም ልጅ በናያስ ከሊታውያንና ፈሊታውያንም ወረዱ፥ ሰሎሞንንም በንጉሡ በዳዊት በቅሎ ላይ አስቀምጠው ወደ ግዮን አመጡት።


አስተዳዳሪ ለሐሰተኛ ነገር ትኩረት ቢሰጥ፥ ከእርሱ በታች ያሉት ሁሉ ዓመፀኞች ይሆናሉ።


“ሥርዓቴን ጠብቁ። እንስሳህን ከሌላ ዓይነት ዘር ጋር አታዳቅል፤ በእርሻህም ሁለት ዓይነት ዘር አትዝራ፤ ከሁለት ዓይነት ነገር የተሠራ ልብስ አትልበስ።”


እጆቻቸው ክፉ ለማድረግ የተለማመዱ ናቸው፤ ልዑሉና ፈራጁ ጉቦን ይፈልጋሉ፥ ትልቁም ሰው እንደ ነፍሱ ምኞት ይናገራል፤ እንዲሁም ክፋትን ይጐነጉናሉ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች