2 ነገሥት 9:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)5 እዚያም እንደ ደረሰ የጦር መኰንኖች ተቀምጠው ሲወያዩ አግኝቶ “ጌታዬ ለአንተ የምሰጥህ መልእክት አለኝ” አለው። ኢዩም “ከእኛ መካከል ለማንኛችን ነው የምትናገረው?” ሲል ጠየቀው። ነቢዩም “የምናገረው ለአንተው ነው” ሲል መለሰ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም5 በዚያ እንደ ደረሰም፣ የሰራዊቱ ጦር መኰንኖች በአንድነት ተቀምጠው ነበር፤ እርሱም “መኰንን ሆይ፤ ወደ አንተ ተልኬአለሁ” አለ። ኢዩም፣ “ለማንኛችን ነው?” ሲል ጠየቀ። እርሱም፣ “መኰንን ሆይ፤ ለአንተ ነው” ብሎ መለሰ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም5 እዚያም እንደ ደረሰ የጦር መኰንኖች ተቀምጠው ሲወያዩ አግኝቶ “ጌታዬ ለአንተ የምሰጥህ መልእክት አለኝ” አለው። ኢዩም “ከእኛ መካከል ለማንኛችን ነው የምትናገረው?” ሲል ጠየቀው። ነቢዩም “የምናገረው ለአንተው ነው” ሲል መለሰ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)5 በገባም ጊዜ፥ እነሆ፥ የሠራዊት አለቆች ተቀምጠው አገኘ፤ እርሱም፥ “አለቃ ሆይ፥ የምናገረው መልእክት አለኝ” አለ። ኢዩም፥ “ከማንኛችን ጋር ነው?” አለ። እርሱም፥ “አለቃ ሆይ፥ ከአንተ ጋር ነው” አለ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)5 በገባም ጊዜ፥ እነሆ፥ የሠራዊት አለቆች ተቀምጠው ነበር፤ እርሱም “አለቃ ሆይ! ለአንተ መልእክት አለኝ፤” አለ። ኢዩም “ለማንኛችን ነው?” አለ። እርሱም “አለቃ ሆይ! ለአንተ ነው፤” አለ። ምዕራፉን ተመልከት |