2 ነገሥት 8:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)9 ስለዚህም አዛሄል በደማስቆ ከሚገኘው ምርጥ የምድር በረከት ሁሉ በአርባ ግመሎች ጭኖ ወደ ኤልሳዕ ሄደ፤ አዛሄልም ኤልሳዕን ባገኘው ጊዜ “ልጅህ ንጉሥ ቤንሀዳድ ከሕመሙ ይድን ወይም አይድን እንደሆነ እንድትነግረው እጠይቅህ ዘንድ ልኮኛል” አለው። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም9 አዛሄልም ደማስቆ ካፈራቻቸው ምርጥ ነገሮች ሁሉ የአርባ ግመል ጭነት ገጸ በረከት ይዞ ኤልሳዕን ለመገናኘት ሄደ። ሄዶም ፊቱ ቆመና፣ “የሶርያ ንጉሥ ልጅህ ቤን ሃዳድ፣ ‘ከዚህ በሽታ እድናለሁን?’ ሲል ወደ አንተ ልኮኛል” አለው። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም9 ስለዚህም አዛሄል በደማስቆ ከሚገኘው ምርጥ የምድር በረከት ሁሉ በአርባ ግመሎች ጭኖ ወደ ኤልሳዕ ሄደ፤ አዛሄልም ኤልሳዕን ባገኘው ጊዜ “ልጅህ ንጉሥ ቤንሀዳድ ከሕመሙ ይድን ወይም አይድን እንደ ሆነ እንድትነግረው እጠይቅህ ዘንድ ልኮኛል” አለው። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)9 አዛሄልም ሊገናኘው ሄደ፤ ከእርሱም ጋር ከደማስቆ መልካሙን ነገር ሁሉ የአርባ ግመል ጭነት ገጸ በረከት ወሰደ፤ መጥቶም በፊቱ ቆመና፥ “ልጅህ የሶርያ ንጉሥ ወልደ አዴር፦ ከዚህ በሽታ እድናለሁን? ሲል ወደ አንተ ልኮኛል” አለው። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)9 አዛሄልም ሊገናኘው ሄደ፤ ከእርሱም ጋር ከደማስቆ መልካሙን ነገር ሁሉ የአርባ ግመል ጭነት ገጸ በረከት ወሰደ፤ መጥቶም በፊቱ ቆመና “ልጅህ የሶርያ ንጉሥ ቤንሀዳድ ‘ከዚህ በሽታ እድናለሁን?’ ሲል ወደ አንተ ልኮኛል፤” አለ። ምዕራፉን ተመልከት |