Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ነገሥት 8:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ባለሟሎቹ ከሆኑት ባለ ሥልጣኖች አንዱ የሆነውን አዛሄልን ጠርቶ፥ “ለነቢዩ ስጦታ ይዘህ ሂድና እኔ ከዚህ በሽታ እድን ወይም አልድን እንደሆነ እግዚአብሔርን እንዲጠይቅልኝ ለምነው” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ንጉሡም አዛሄልን፣ “ገጸ በረከት ይዘህ ሂድና የእግዚአብሔርን ሰው ተገናኘው። በርሱም አማካይነት፣ ‘ከዚህ በሽታ እድናለሁን?’ ብለህ እግዚአብሔርን ጠይቅ” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ባለሟሎቹ ከሆኑት ባለሥልጣኖች አንዱ የሆነውን አዛሄልን ጠርቶ፥ “ለነቢዩ ስጦታ ይዘህ ሂድና እኔ ከዚህ በሽታ እድን ወይም አልድን እንደ ሆነ እግዚአብሔርን እንዲጠይቅልኝ ለምነው” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ንጉ​ሡም አዛ​ሄ​ልን፥ “ገጸ በረ​ከት በእ​ጅህ ወስ​ደህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሰው ተቀ​በ​ለው፤ ከዚ​ህም በሽታ እድን እንደ ሆነ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ጠይ​ቀው” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ንጉሡም አዛሄልን “ገጸ በረከት በእጅህ ወስደህ የእግዚአብሔርን ሰው ልትገናኝ ሂድ፤ በእርሱም አፍ ‘ከዚህ በሽታ እድናለሁን?’ ብለህ እግዚአብሔርን ጠይቅ፤” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ነገሥት 8:8
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በዚህም ጊዜ የእስራኤል ንጉሥ አካዝያስ በሰማርያ ቤተ መንግሥቱ ሳለ ከሰገነቱ ላይ ወድቆ በብርቱ ስለ ቆሰለ ታሞ ነበር፤ እርሱም “እኔ ከዚህ ሕመም እድን ወይም አልድን እንደሆነ በፍልስጥኤም የዔክሮን ከተማ አምላክ የሆነውን ብዔልዜቡልን ጠይቃችሁልኝ ኑ” ብሎ መልእክተኞቹን ላከ።


ጌታም እንዲህ አለው፤ “በደማስቆ ከተማ አጠገብ ወደሚገኘው በረሓ ተመልሰህ ሂድ፤ እዚያም በደረስህ ጊዜ አዛሄልን ቀብተህ በሶርያ ላይ አንግሠው።


ሳኦልም አገልጋዩን፥ “ብንሄድስ ለሰውየው ምን እንሰጠዋለን? በስልቻዎቻችን የያዝነው ስንቅ አልቋአል፤ ለዚያ የእግዚአብሔር ሰው የምንሰጠው ስጦታ የለንም፤ ምን አለን?” አለው።


ወደ ውጭም አውጥቶ “ጌቶች ሆይ! እድን ዘንድ ምን ማድረግ ይገባኛል?” ኣላቸው።


አንድ ሰውም “ጌታ ሆይ! የሚድኑ ጥቂቶች ናቸውን?” አለው። እርሱም እንዲህ አላቸው፦


ንጉሡም “ይህን ደብዳቤ ይዘህ ወደ እስራኤል ንጉሥ ሂድ” ብሎ ፈቀደለት። ስለዚህም ንዕማን ሠላሳ ሺህ ጥሬ ብር፥ ስድስት ሺህ መሐለቅ ወርቅና ምርጥ የሆነ ዐሥር መለወጫ ልብስ አስጭኖ፥ ጉዞውን ቀጠለ፤


እነርሱም እንዲህ ሲሉ መለሱለት፤ “አንድ ሰው በመንገድ አግኝቶን ወደ አንተ ተመልሰን እንድንመጣና እግዚአብሔር ስለ አንተ የተናገረውን እንድናስረዳህ አዘዘን፤ እርሱም እንዲህ የሚል ነው፤ ‘የዔክሮንን አምላክ ብዔልዜቡልን ለመጠየቅ መልእክተኞች የላክህበት ምክንያት ምንድነው? በእስራኤል ዘንድ አምላክ የለም ብለህ በማሰብህ ነውን? ስለዚህ ትሞታለህ እንጂ ከዚህ ሕመም አትፈወስም! ከተኛህበትም አልጋ አትነሣም!’”


ከአዛሄል እጅ ከመገደል ተርፎ የሚያመልጠውን ማንኛውንም ሰው ኢዩ ይገድለዋል፤ ከኢዩ እጅ የሚያመልጠውንም ኤልሳዕ ይገድለዋል።


“እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፤ ‘በእስራኤል አምላክ እንደሌለ በመቁጠር፥ የዔክሮንን አምላክ ብዔልዜቡልን እንዲጠይቁልህ መልእክተኞች በመላክህ ምክንያት ትሞታለህ እንጂ አትድንም!’” አለው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች