2 ነገሥት 4:41 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)41 ኤልሳዕም ዱቄት እንዲሰጡት ጠይቆ በድስቱ ውስጥ ጨመረውና “ወጡን እያወጣህ ጨምርላቸው” ሲል አዘዘ፤ በዚህም ጊዜ በወጡ ውስጥ ምንም ዓይነት መራራነት አልነበረም። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም41 ኤልሳዕም፣ “እስኪ ዱቄት አምጡልኝ” አለ። ያንም በምንቸቱ ውስጥ ጨምሮ፣ “እንዲመገቡት ለሰዎቹ አቅርቡላቸው” አለ። በምንቸቱም ውስጥ ጕዳት የሚያስከትል ነገር አልተገኘም። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም41 ኤልሳዕም ዱቄት እንዲሰጡት ጠይቆ በድስቱ ውስጥ ጨመረውና “ወጡን እያወጣህ ጨምርላቸው” ሲል አዘዘ፤ በዚህም ጊዜ በወጡ ውስጥ ምንም ዐይነት መራራነት አልነበረም። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)41 ኤልሳዕም፥ “ዶቄት አምጣና በምንቸቱ ውስጥ ጨምረው” አለው፥ ኤልሳዕም ግያዝን፥ “ለሕዝቡ መልስላቸው ይብሉ” አለው። ከዚህም በኋላ በምንቸቱ ውስጥ ክፉ ነገር አልተገኘም። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)41 እርሱም “ዱቄት አምጡልኝ፤” አለ፤ በምንቸቱም ውስጥ ጥሎ “ይበሉ ዘንድ ለሕዝቡ ቅዱ፤” አለ። በምንቸቱም ውስጥ ክፉ ነገር አልተገኘም። ምዕራፉን ተመልከት |