2 ነገሥት 4:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)4 ከዚህም በኋላ አንቺና ልጆችሽ ወደ ቤት ገብታችሁ መዝጊያውን ዝጉ፤ የማሰሮውንም ዘይት ወደ ማድጋዎቹ ማንቆርቆር ጀምሩ፤ እያንዳንዱ ማድጋ በሚሞላበት ጊዜ ለብቻው በማግለል አኑሩት።” ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም4 ገብተሽም መዝጊያውን በአንቺና በልጆችሽ ላይ የኋሊት ዝጊው፤ ዘይቱንም በማድጋዎቹ ሁሉ ጨምሪ፤ እያንዳንዱ ማድጋ ሲሞላም ወደ አንድ በኩል አኑሪው።” ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም4 ከዚህም በኋላ አንቺና ልጆችሽ ወደ ቤት ገብታችሁ መዝጊያውን ዝጉ፤ የማሰሮውንም ዘይት ወደ ማድጋዎቹ ማንቈርቈር ጀምሩ፤ እያንዳንዱ ማድጋ በሚሞላበት ጊዜ ለብቻው በማግለል አኑሩት።” ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)4 ወደ ቤትሽም ገብተሽ ከአንቺና ከልጆችሽ በኋላ በሩን ዝጊ፤ ወደ እነዚህም ማድጋዎች ሁሉ ዘይቱን ገልብጪ፤ የሞላውንም ፈቀቅ አድርጊ” አላት። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)4 ገብተሽም ከአንቺና ከልጆችሽ በኋላ በሩን ዝጊ፤ ወደ እነዚህም ማድጋዎች ሁሉ ዘይቱን ገልብጪ፤ የሞላውንም ፈቀቅ አድርጊ፤” አለ። ምዕራፉን ተመልከት |