2 ነገሥት 4:38 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)38 በመላ አገሪቱ ራብ በነበረበት በአንድ ወቅት ኤልሳዕ ወደ ጌልጌላ ተመልሶ መጣ፤ በዚያም የነቢያትን ጉባኤ በማስተማር ላይ ሳለ አገልጋዩን “ትልቅ ድስት ጥደህ ወጥ ሥራላቸው” አለው። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም38 ኤልሳዕ ወደ ጌልገላ ተመለሰ፤ በዚያም አገር ራብ ነበረ። የነቢያት ማኅበር በፊቱ ተቀምጠው ሳለ አገልጋዩን፣ “ትልቁን ምንቸት ጣድና ለእነዚህ ሰዎች ወጥ ሥራላቸው” አለው። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም38 በመላ አገሪቱ ራብ በነበረበት በአንድ ወቅት ኤልሳዕ ወደ ጌልጌላ ተመልሶ መጣ፤ በዚያም የነቢያትን ጉባኤ በማስተማር ላይ ሳለ አገልጋዩን “ትልቅ ድስት ጥደህ ወጥ ሥራላቸው” አለው። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)38 ኤልሳዕም ዳግመኛ ወደ ጌልጌላ ተመለሰ፤ በምድርም ላይ ራብ ነበረ፤ የነቢያትም ልጆች በፊቱ ተቀምጠው ነበር፤ ኤልሳዕም ሎሌውን፥ “ታላቁን ምንቸት ጣድ፤ ለነቢያትም ልጆች ቅጠላ ቅጠል አብስልላቸው” አለው። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)38 ኤልሳዕም ዳግመኛ ወደ ጌልገላ መጣ፤ በምድርም ላይ ራብ ነበረ፤ የነቢያትም ልጆች በፊቱ ተቀምጠው ነበር፤ ሎሌውንም “ታላቁን ምንቸት ጣድ፤ ለነቢያት ልጆችም ወጥ ሥራ፤” አለው። ምዕራፉን ተመልከት |