Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ነገሥት 3:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 የሞዓብ ንጉሥ ሜሻዕ በግ አርቢ ነበር፤ በየዓመቱም አንድ መቶ ሺህ ጠቦትና የአንድ መቶ ሺህ በጎች ጠጉር ለእስራኤል ንጉሥ ይገብር ነበር፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 በዚህ ጊዜ የሞዓብ ንጉሥ ሞሳ በግ ያረባ ነበር፤ እርሱም መቶ ሺሕ ጠቦትና የመቶ ሺሕ አውራ በግ ጠጕር ለእስራኤል ንጉሥ ይገብር ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 የሞአብ ንጉሥ ሜሻዕ በግ አርቢ ነበር፤ በየዓመቱም አንድ መቶ ሺህ ጠቦትና የአንድ መቶ ሺህ በጎች ጠጒር ለእስራኤል ንጉሥ ይገብር ነበር፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 የሞ​ዓ​ብም ንጉሥ ሞሳ ባለ በጎች ነበር፤ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ መቶ ሺህ የጠ​ጕር አውራ በጎ​ች​ንና መቶ ሺህ ጠቦ​ቶ​ችን ይገ​ብ​ር​ለት ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 የሞዓብም ንጉሥ ሞሳ በግ አርቢ ነበረ፤ ለእስራኤልም ንጉሥ የመቶ ሺህ ጠቦትና የመቶ ሺህ አውራ በጎች ጠጕር ይገብርለት ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ነገሥት 3:4
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አብራምም በከብት በብርና በወርቅ እጅግ በለጠገ።


እንዲሁም ዳዊት ሞዓባውያንን ድል አደረገ፤ በመሬት ላይ አጋድሞ በገመድ ለካቸው፤ በገመድ ከተለኩትም ሁለት እጅ ሲገድል፥ አንድ እጅ ግን በሕይወት ይተው ነበር። ስለዚህ ሞዓባውያን የዳዊት ተገዢዎች ሆኑ፤ ገበሩለትም።


ከዚያም የደማስቆ ክፍል በሆነው የሶርያውያን ግዛት የጦር ሰፈሮችን አቋቋመ። ሶርያውያን ተገዙለት፤ ገበሩለትም። ጌታም ዳዊት በሄደበት ሁሉ ድልን ሰጠው።


ሞዓብን መታ፤ ሞዓባውያንም ለዳዊት ገባሮች ሆኑ፥ ግብርም አመጡለት።


ብዙም እንስሶች ነበሩትና በምድረ በዳውና በቈላው በደጋውም ግንብ ሠራ፥ ብዙ ጉድጓድም ማሰ፤ ደግሞም እርሻ ይወድድ ነበርና በተራራማውና በፍሬያማው ስፍራ አራሾችና አትክልተኞች ነበሩት።


ሰባት ሺህ በጎች፥ ሦስት ሺህ ግመሎች፥ አምስት መቶ ጥማድ በሬዎች፥ አምስት መቶ እንስት አህዮችና እጅግ ብዙም አገልጋዮች ነበሩት። ያም ሰው በምሥራቅ ካሉ ሰዎች ሁሉ ይልቅ ታላቅ ነበረ።


ጌታም ከፊተኛው ይልቅ የኋለኛውን ለኢዮብ ባረከ፥ ዐሥራ አራት ሺህም በጎች፥ ስድስት ሺህም ግመሎች፥ አንድ ሺህም ጥማድ በሬዎች፥ አንድ ሺህም እንስት አህዮች ነበሩት።


እግዚአብሔር በቅድስናው ተናገረ፥ “በድል መንፈስ፥ ሴኬምንም እከፋፍላለሁ፥ የሱኮትንም ሸለቆ እለካለሁ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች