2 ነገሥት 3:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)13 ኤልሳዕም የእስራኤልን ንጉሥ ኢዮራምን፥ “እኔ አንተን የምረዳህ ስለምንድን ነው? ሄደህ አባትህና እናትህ ይጠይቁአቸው የነበሩትን እነዚያን ነቢያት ጠይቅ!” አለው። ንጉሥ ኢዮራምም መልሶ፥ “አይደለም እኮ! ሦስታችንንም ነገሥታት ለሞዓብ ንጉሥ አሳልፎ ለመስጠት የጠራን እግዚአብሔር ነው” አለ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም13 ኤልሳዕም የእስራኤልን ንጉሥ፤ “ከአንተ ጋራ ምን የሚያገናኘን ጕዳይ አለና መጣህ፤ አሁን የአባትህና የእናትህ ነቢያት ወዳሉበት ሂድ” አለው። የእስራኤልም ንጉሥ መልሶ፣ “ይህማ አይሆንም፤ በሞዓብ እጅ አሳልፎ ሊሰጠን እኛን ሦስት ነገሥታት አንድ ላይ የጠራን እግዚአብሔር ነው” አለ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም13 ኤልሳዕም የእስራኤልን ንጉሥ ኢዮራምን፥ “እኔ አንተን የምረዳህ ስለምንድን ነው? ሄደህ አባትህና እናትህ ይጠይቁአቸው የነበሩትን እነዚያን ነቢያት ጠይቅ!” አለው። ንጉሥ ኢዮራምም መልሶ፥ “አይደለም እኮ! ሦስታችንንም ነገሥታት ለሞአብ ንጉሥ አሳልፎ ለመስጠት የጠራን እግዚአብሔር ነው” አለ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)13 ኤልሳዕም የእስራኤልን ንጉሥ፥ “እኔ ከአንተ ጋር ምን አለኝ? ወደ አባትህ ነቢያትና ወደ እናትህ ነቢያት ሂድ፥” አለው። የእስራኤልም ንጉሥ፥ “አይደለም፤ በሞዓብ እጅ ይጥላቸው ዘንድ እግዚአብሔር እነዚህን ሦስት ነገሥታት ጠርቶአልን?” አለው። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)13 ኤልሳዕም የእስራኤልን ንጉሥ “እኔ ከአንተ ጋር ምን አለኝ? ወደ አባትህና ወደ እናትህ ነቢያት ሂድ፤” አለው። የእስራኤልም ንጉሥ “አይደለም፥ በሞዓብ እጅ ይጥላቸው ዘንድ እግዚአብሔር እነዚህን ሦስት ነገሥታት ጠርቶአል፤” አለው። ምዕራፉን ተመልከት |