Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ነገሥት 19:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ከዚህ በኋላ የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ ወደ ንጉሥ ሕዝቅያስ እንዲህ የሚል መልእክት ላከ፦ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ስለ አሦር ንጉሠ ነገሥት ስለ ሰናክሬም ዛቻ ያቀረብከውን ጸሎት ሰምቻለሁ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ከዚህ በኋላ የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ ወደ ሕዝቅያስ እንዲህ ሲል መልእክት ላከ፤ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘በአሦር ንጉሥ በሰናክሬም ላይ ወደ እኔ ያቀረብኸውን ልመና ሰምቻለሁ’

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ከዚህ በኋላ የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ ወደ ንጉሥ ሕዝቅያስ እንዲህ የሚል መልእክት ላከ፦ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ስለ አሦር ንጉሠ ነገሥት ስለ ሰናክሬም ዛቻ ያቀረብከውን ጸሎት ሰምቻለሁ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 የአ​ሞ​ጽም ልጅ ኢሳ​ይ​ያስ እን​ዲህ ብሎ ወደ ሕዝ​ቅ​ያስ ላከ፥ “የሠ​ራ​ዊት ጌታ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ስለ አሦር ንጉሥ ስለ ሰና​ክ​ሬም ወደ እኔ የለ​መ​ን​ኸ​ውን ሰም​ቻ​ለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 የአሞጽም ልጅ ኢሳይያስ እንዲህ ብሎ ወደ ሕዝቅያስ ላከ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ‘ስለ አሦር ንጉሥ ስለ ሰናክሬም ወደ እኔ የለመንኽውን ሰምቻለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ነገሥት 19:20
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“ሕዝቤን ወደሚመራው ወደ ንጉሥ ሕዝቅያስ ተመልሰህ በመግባት እንዲህ በለው፦ ‘እኔ የቀድሞ አባትህ የዳዊት አምላክ እግዚአብሔር ጸሎትህን ሰምቻለሁ፤ እንባህንም ተመልክቻለሁ፤ እኔ እፈውስሃለሁ፤ ከሦስት ቀንም በኋላ ወደ ቤተ መቅደስ ትወጣለህ፤


‘ቆርኔሌዎስ ሆይ! በእግዚአብሔር ፊት ጸሎትህ ተሰማ ምጽዋትህም ታሰበ።


ወደ እኔ ተጣራ፥ እኔም እመልስልሃለሁ፤ አንተም የማታውቃቸውን ታላላቅና ስውር የሆኑ ነገሮችን እነግርሃለሁ።


እንዲህም ይሆናል፤ ሳይጠሩ እመልስላቸዋለሁ፥ ገናም ሲናገሩ እሰማለሁ።


እርሱም ትኩር ብሎ ሲመለከተው ደንግጦ “ጌታ ሆይ! ምንድነው?” አለ። መልአኩም አለው “ጸሎትህና ምጽዋትህ በእግዚአብሔር ፊት ለመታሰቢያ እንዲሆን አረገ።


ሁልጊዜም እንደምትሰማኝ አወቅሁ፤ ነገር ግን አንተ እንደ ላክኸኝ ያምኑ ዘንድ በዚህ ዙሪያ ስለ ቆሙት ሕዝብ ተናገርሁ፤”


አኪጦፌልም ምክሩን እንዳልተከተሉት ባየ ጊዜ፥ አህያውን ጭኖ ቤቱ ወደሚገኝበት ወደ መኖሪያ ከተማው ሄደ፤ ቤቱንም አስተካክሎ በገዛ እጁ ታነቀ፤ ከሞተ በኋላ በአባቱም መቃብር ተቀበረ።


በዚህ ጊዜ፥ “ከአቤሴሎም ጋር ካሤሩት መካከል አንዱ አኪጦፌል ነው” ብለው ለዳዊት ነገሩት። ዳዊትም፥ “ጌታ ሆይ! እባክህን የአኪጦፌልን ምክር ወደ ከንቱነት ለውጠው” ሲል ጸለየ።


የዚያን ጊዜ ትጠራለህ ጌታም ይሰማሃል፤ ትጮኻለህ እርሱም፦ እነሆኝ ይላል። ከመካከልህ ቀንበርን ብታርቅ፥ በጣትህም መጠቆም ብትተው፥ ባታንጐራጉርም፥


በመከራ ቀን ጥራኝ፥ አድንህማለሁ አንተም ታከብረኛለህ።


ወደ እርሱም ትጸልያለህ፥ እርሱም ይሰማሃል፥ ስእለትህንም ትሰጣለህ።


አቤቱ፥ በጽዮን ለአንተ ምስጋና ይገባል፥ ለአንተም ስእለት ይቀርባል።


ሕዝቅያስ በነገሠ በዐሥራ አራተኛው ዓመት የአሦር ንጉሠ ነገሥት ሰናክሬም አደጋ በመጣል የተመሸጉትን የይሁዳን ከተሞች ያዘ፤


ጸሎትን ወደምትሰማ ወደ አንተ ሥጋ ሁሉ ይመጣል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች