Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ነገሥት 18:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 አሁንም በንጉሠ ነገሥቱ ስም ለፍልሚያ እጠይቅሃለሁ፤ መጋለብ የሚችሉ በቂ ሰዎች ታገኝ እንደሆነ እስቲ ሁለት ሺህ ፈረሶች ልስጥህ!

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 “ ‘አሁን ናና፣ ከጌታዬ ከአሦር ንጉሥ ጋራ ተደራደር፤ የሚጋልቧቸው ሰዎች ካሉህ፣ ሁለት ሺሕ ፈረሶች እሰጥሃለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 አሁንም በንጉሠ ነገሥቱ ስም ለፍልሚያ እጠይቅሃለሁ፤ መጋለብ የሚችሉ በቂ ሰዎች ታገኝ እንደ ሆነ እስቲ ሁለት ሺህ ፈረሶች ልስጥህ!

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 አሁ​ንም እን​ግ​ዲህ ከጌ​ታዬ ከአ​ሦር ንጉሥ ጋር ተወ​ራ​ረድ፤ የሚ​ቀ​መ​ጡ​ባ​ቸ​ው​ንም ሰዎች ማግ​ኘት ቢቻ​ልህ እኔ ሁለት ሺህ ፈረ​ሶች እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 አሁን እንግዲህ ከጌታዬ ከአሦር ንጉሥ ጋር ተወራረድ፤ የሚቀመጡባቸውንም ሰዎች ማግኘት ቢቻልህ እኔ ሁለት ሺህ ፈረሶች እሰጥሃለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ነገሥት 18:23
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ቤንሀዳድም “በሰማርያ ለያንዳንዱ ወታደር አንዳንድ ጭብጥ ዐፈር ሊዳረስ እስከማይችል ድረስ ብዙ ወታደሮችን ባላሰልፍ አማልክት ይቅሠፉኝ!” ብሎ የዛቻ መልእክቱን መልሶ ላከበት።


ቤንሀዳድም “ቃፊሮቹ አመጣጣቸው ለጦርነትም ይሁን ለሰላም፥ ከነሕይወታቸው ይዛችሁ አምጡልኝ” ሲል አዘዘ።


የአሦር የጦር አዛዥ ንግግሩን በመቀጠል እንደገና እንዲህ አለ፦ “አምላክህ እግዚአብሔር እንደሚረዳህ አድርገህ ታስባለህን? ይህማ እንዳይሆን፥ አንተ የእግዚአብሔርን የተቀደሱ ስፍራዎችንና መሠዊያዎችን ደምስሰህ ‘የይሁዳና የኢየሩሳሌም ሕዝብ ማምለክ የሚገባቸው ኢየሩሳሌም ውስጥ በሚገኘው በአንድ መሠዊያ ብቻ ነው’ ብለህ ወስነሃል።


አንተ እኮ እጅግ በጣም ዝቅተኛ ከሆነው ከአሦር ተራ የጦር መኰንን ጋር እንኳ መወዳደር አትችልም፤ ግብጻውያን ሠረገሎችንና ፈረሶችን ይልኩልኛል ብለህ የምትጠባበቀውም በዚሁ ምክንያት ነው።


እርሱም ዳዊትን ትኩር ብሎ ሲያየው፥ ደም ግባት ያለው፥ መልከ መልካምና ልጅ ነበር፤ ስለዚህ በንቀት ዐይን ተመለከተው።


እርሱም ዳዊትን፥ “እስቲ ወደኔ ና! ሥጋህን ለሰማይ አሞሮችና፥ ለምድር አራዊት እሰጣለሁ” አለው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች