Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ነገሥት 18:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ከዚያም በኋላ ወደ ሕዝቅያስ መልእክት ላኩበት፤ ሕዝቅያስም ባለሟሎቹ የሆኑ ሦስት ባለ ሥልጣኖች ሄደው እንዲገናኙአቸው አዘዘ፤ እነርሱም የቤተ መንግሥቱ ኃላፊ የሆነ የሒልቂያ ልጅ ኤልያቄም፥ እንዲሁም የቤተ መንግሥት ጸሐፊ የሆነው ሼብናና የቤተ መዛግብት ኃላፊ የሆነው የአሳፍ ልጅ ዮአሕ ነበሩ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ወደ ንጉሡም ላኩበት፤ ከዚያም የቤተ መንግሥቱ አዛዥ፣ የኬልቅያስ ልጅ ኤልያቄም፣ ጸሓፊው ሳምናስ፣ ታሪክ መዝጋቢውም የአሳፍ ልጅ ዮአስ ወደ እነርሱ ሄዱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ከዚያም በኋላ ወደ ሕዝቅያስ መልእክት ላኩበት፤ ሕዝቅያስም ባለሟሎቹ የሆኑ ሦስት ባለሥልጣኖች ሄደው እንዲገናኙአቸው አዘዘ፤ እነርሱም የቤተ መንግሥቱ ኀላፊ የሆነ የሒልቂያ ልጅ ኤልያቄም፥ እንዲሁም የቤተ መንግሥት ጸሐፊ የሆነው ሼብናና የቤተ መዛግብት ኀላፊ የሆነው የአሳፍ ልጅ ዮአሕ ነበሩ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ሕዝ​ቅ​ያ​ስ​ንም ጠሩ፤ የቤ​ቱም አዛዥ የኬ​ል​ቅዩ ልጅ ኤል​ያ​ቄም ጸሓ​ፊ​ውም ሳም​ናስ ታሪክ ጸሓ​ፊ​ውም የአ​ሳፍ ልጅ ዮአስ ወደ እነ​ርሱ ወጡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ንጉሡንም ጠሩ፤ የቤቱም አዛዥ የኬልቅያስ ልጅ ኤልያቄም ጸሐፊውም ሳምናስ ታሪክ ጸሐፊውም የአሳፍ ልጅ ዮአስ ወደ እነርሱ ወጡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ነገሥት 18:18
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አዶራም በግዳጅ ሥራ ላይ ለተሰማሩት ሰዎች አለቃ ሲሆን፤ የአሒሉድ ልጅ ኢዮሣፍጥ ደግሞ ታሪክ ጸሓፊ ነበር፤


ኤሊሖሬፍና አኪያ የተባሉት የሺሻ ልጆች፥ የቤተ መንግሥት ጸሐፊዎች፤ ኢዮሣፍጥ የተባለው የአሒሉድ ልጅ፥ ታሪክ ጸሐፊና የመዛግብት ኀላፊ።


ከዚህም በኋላ ኤልያቄምና፥ ሼብና እንዲሁም ዮአሕ ይህን የጦር አዛዥ “ፍቹን ስለምናውቅ በሶርያ ቋንቋ እንድትነግረን እንለምንሃለን፤ በቅጽር ላይ ያሉት ሕዝብ ሁሉ በሚሰሙት በዕብራይስጥ ቋንቋ አትናገረን” አሉት።


ከዚህ በኋላ ኤልያቄምና ሼብና እንዲሁም ዮአሕ በኀዘን ልብሳቸውን ቀደዱ፤ ወደ ንጉሥ ሕዝቅያስ ቀርበው የአሦራውያን ባለ ሥልጣን የተናገረውን አስረዱት።


ወዲያውም የቤተ መንግሥቱ ኃላፊ የሆነውን ኤልያቄምን፥ የቤተ መንግሥቱን ጸሐፊ ሼብናንና ሽማግሌዎች ካህናትን ወደ አሞጽ ልጅ ወደ ነቢዩ ኢሳይያስ ላከ፤ እነርሱም ራሳቸው ማቅ ለብሰው ነበር፤


በነገሠም በዓሥራ ስምንተኛው ዓመት ምድሪቱንና የጌታን ቤት ካነጻ በኋላ፥ የኤዜልያስ ልጅ ሳፋን፥ የከተማይቱም አለቃ መዕሤያ፥ ታሪክ ጸሐፊም የኢዮአካዝ ልጅ ኢዮአክ የጌታን የአምላኩን ቤት እንዲጠግኑ ላካቸው።


እነሆ፥ ኃይለኞቻቸው በሜዳ ይጮኻሉ፤ የሰላም መልእክተኞች መራራ ልቅሶ ያለቅሳሉ።


የቤተ መንግሥቱ አዛዥ የኬልቅያስ ልጅ ኤልያቄም፥ ጸሐፊውም ሳምናስ፥ ታሪክ ጸሐፊው የአሳፍ ልጅ ዮአስ፥ ልብሳቸውን ቀደው ወደ ሕዝቅያስ መጡ፤ የራፋስቂስንም ቃል ነገሩት።


የቤተ መንግሥቱ አዛዥ የኤልቅያስ ልጅ ኤልያቄም፥ ጸሐፊውም ሳምናስ፥ ታሪክ ጸሐፊው የአሳፍ ልጅ ዮአስ፥ ወደ እርሱ መጡ።


የቤቱንም አዛዥ ኤልያቄምን ጸሐፊውንም ሳምናስን የካህናቱንም ሽማግሌዎች ማቅ ለብሰው ወደ ነቢዩ ወደ አሞጽ ልጅ ወደ ኢሳይያስ እንዲሄዱ ላካቸው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች