Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ነገሥት 17:31 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

31 የዓዋ ሕዝብ ኒብሐዝና ታርታቅ ተብለው በሚጠሩ አማልክታቸው ስም ጣዖቶቻቸውን ሠሩ፤ የሰፋርዋይምም ሕዝብ አድራሜሌክና ዓናሜሌክ ተብለው ለሚጠሩ አማልክቶቻቸው ልጆቻቸውን የሚቃጠል መሥዋዕት አድርገው አቀረቡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

31 አዋውያንም ኤልባዝርንና ተርታቅ የተባሉትን አማልክት ሲሠሩ፣ ከሴፈርዋይም የመጡት ደግሞ አድራሜሌክና አናሜሌክ ለተባሉት አማልክታቸው ልጆቻቸውን የሚቃጠል መሥዋዕት አድርገው አቀረቡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

31 የዓዋ ሕዝብ ኒብሐዝና ታርታቅ ተብለው በሚጠሩ አማልክታቸው ስም ጣዖቶቻቸውን ሠሩ፤ የሰፋርዋይምም ሕዝብ አድራሜሌክና ዓናሜሌክ ተብለው ለሚጠሩ አማልክቶቻቸው ልጆቻቸውን የሚቃጠል መሥዋዕት አድርገው አቀረቡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

31 የሐ​ማ​ትም ሰዎች አሲ​ማ​ትን ሠሩ፤ አዋ​ው​ያ​ንም ኤል​ባ​ዝ​ር​ንና ተር​ታ​ቅን ሠሩ፤ የሴ​ፌ​ር​ዋ​ይም ሰዎች ለሴ​ፌ​ር​ዋ​ይም አማ​ል​ክት ለአ​ድ​ራ​ሜ​ሌ​ክና ለአ​ኔ​ሜ​ሌክ ልጆ​ቻ​ቸ​ውን በእ​ሳት ይሠዉ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

31 አዋውያንም ኤልባዝርንና ተርታቅን ሠሩ፤ የሴፈርዋይም ሰዎችም ለሴፈርዋይም አማልክት ለአድራሜሌክና ለአነሜሌክ ልጆቻቸውን በእሳት ያቃጥሉ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ነገሥት 17:31
8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ለእነዚያም አሕዛብ አማልክት ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን የሚቃጠል መሥዋዕት አድርገው አቀረቡ፤ ከሙታን ጠሪዎችና ከጠንቋዮችም ምክር ጠየቁ፤ እግዚአብሔር ለሚጠላው ክፉ ነገር ሁሉ ራሳቸውን አሳልፈው በመስጠት የእግዚአብሔርን ቁጣ አነሣሡ።


የአሦር ንጉሠ ነገሥት በባቢሎን፥ ኩታ፥ ዓዋ፥ ሐማትና ሰፋርዋይም ተብለው በሚጠሩት ከተሞች ይኖሩ የነበሩትን አሕዛብ አምጥቶ ተሰደው በሄዱት በእስራኤላውያን እግር በመተካት በሰማርያ ከተሞች እንዲሰፍሩ አደረገ፤ እነርሱም እነዚህን ከተሞች ወርሰው በዚያ መኖር ጀመሩ።


ከዕለታት በአንዱ ቀን ኒስሮክ በሚል ስም በሚጠራው ባዕድ አምላኩ ቤተ መቅደስ ውስጥ በስግደት ላይ እንዳለ፥ ከልጆቹ ሁለቱ በተለይ አድራሜሌክና ሣሬጼር ተብለው የሚጠሩት በሰይፍ ገደሉት፤ እነርሱም ወደ አራራት አምልጠው ሄዱ፤ በእርሱም እግር ተተክቶ ከልጆቹ አንዱ አስራዶ የተባለው ነገሠ።


አዛዡ ሬሑምና ጸሐፊው ሺምሻይ የቀሩትም ተባባሪዎቻቸው፥ ዳኞቹ፥ ባለሥልጣኖቹ፥ አስተዳዳሪዎቹ፥ ጸሐፍያን፥ የኤርካውያን፥ ባቢሎናውያን፥ ሱሳንካውያን፥ ዴሐውያን፥ ዔላማውያን፥


ለራስህ የሠራሃቸው አማልክትህ ወዴት ናቸው? ይሁዳ ሆይ! አማልክትህ እንደ ከተሞችህ ቍጥር ብዛት እንዲሁ ናቸውና እስቲ ይነሡ በመከራህም ጊዜ ያድኑህ።


ከልጆችህ ማናቸውንም ለሞሌክ በእሳት የሚቀርብ መሥዋዕት አድርገህ አትስጥ፥ በዚህም የአምላክህን ስም አታርክስ፤ እኔ ጌታ ነኝ።


በአምላክህ በጌታ ፊት መልካምና ትክክል የሆነውን ነገር ስለምታደርግ፥ ለአንተና ከአንተም በኋላ ለሚመጡት ልጆችህ ለዘለዓለም መልካም እንዲሆንላችሁ፥ እኔ የምሰጥህን እነዚህን ደንቦች ሁሉ በጥንቃቄ ፈጽማቸው።”


አምላክህን ጌታ በእነርሱ መንገድ ፈጽሞ አታምልክ፤ ምክንያቱም አማልክታቸውን ሲያመልኩ ጌታ የሚጸየፈውን ሁሉንም ዓይነት ነገር ያደርጋሉና፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን እንኳን ለአማልክታቸው መሥዋዕት አድርገው ያቃጥላሉ።”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች