Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ነገሥት 13:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 እግዚአብሔር ግን በቸርነቱ ምሕረትን በማድረግ ረዳቸው እንጂ እንዲደመሰሱ አልፈቀደም፤ ይህንንም ያደረገበት ምክንያት ለአብርሃም፥ ለይስሐቅና ለያዕቆብ የሰጠውን ቃል ኪዳን በማሰብ ሕዝቡን ስላልረሳው ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 እግዚአብሔር ግን ራራላቸው፤ ዐዘነላቸው፤ ፊቱን መለሰላቸው፤ ይህም ከአብርሃም፣ ከይሥሐቅና ከያዕቆብ ጋራ ስለ ገባው ኪዳን ሲል ነው፤ እስከ ዛሬ ድረስ ሊያጠፋቸው አልፈለገም፤ ከፊቱም አላስወገዳቸውም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 እግዚአብሔር ግን በቸርነቱ ምሕረትን በማድረግ ረዳቸው እንጂ እንዲደመሰሱ አልፈቀደም፤ ይህንንም ያደረገበት ምክንያት ለአብርሃም፥ ለይስሐቅና ለያዕቆብ የሰጠውን ቃል ኪዳን በማሰብ ሕዝቡን ስላልረሳው ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ራራ​ላ​ቸው፤ ማራ​ቸ​ውም፤ ከአ​ብ​ር​ሃ​ምና ከይ​ስ​ሐቅ፥ ከያ​ዕ​ቆ​ብም ጋር ስላ​ደ​ረ​ገው ቃል ኪዳን እነ​ር​ሱን ተመ​ለ​ከተ፤ ሊያ​ጠ​ፋ​ቸ​ውም አል​ወ​ደ​ደም፤ ፈጽ​ሞም ከፊቱ አል​ጣ​ላ​ቸ​ውም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 እግዚአብሔር ግን ራራላቸው፤ ማራቸውም፤ ከአብርሃምና ከይስሐቅ ከያዕቆብም ጋር ስላደረገውም ቃል ኪዳን እነርሱን ተመለከተ፤ ሊያጠፋቸውም አልወደደም፤ ፈጽሞም ከፊቱ አልጣላቸውም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ነገሥት 13:23
36 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ጌታም፦ “መንፈሴ በሰው ላይ ለዘለዓለም አይኖርም፥ እርሱ ሥጋ ነውና፥ እድሜውም መቶ ሃያ ዓመት ይሆናል” አለ።


አቤቱ ጌታ፥ አምላኬ ሆይ! ወደ አገልጋይህ ጸሎትና ልመና ተመልከት፤ ዛሬም አገልጋይህ በፊትህ የሚጸልየውን ጸሎትና ጥሪውን ስማ።


የሶርያ ንጉሥ አዛሄል በሞተ ጊዜ፥ በእርሱ እግር ተተክቶ ልጁ ቤንሀዳድ ነገሠ።


ከዚህ በኋላ ኢዮአካዝ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤ እግዚአብሔርም የሶርያ ንጉሥ በእስራኤላውያን ላይ የፈጸመባቸው ግፍ እጅግ ከባድ መሆኑን ተመልክቶ የኢዮአካዝን ጸሎት ሰማ።


እግዚአብሔር የእስራኤላውያንን አሠቃቂ መከራ ተመለከተ፤ በእስራኤል ውስጥ ባርያዎችም ሆኑ ነጻ ሰዎች፥ ረዳት አልነበራቸውም።


ይሁን እንጂ እነርሱ ለዘለዓለም ፈጽሞ እንዲደመሰሱ ደግሞ የእግዚአብሔር ፈቃድ አልነበረም፤ ስለዚህም በዳግማዊ ኢዮርብዓም አማካይነት አዳናቸው።


እግዚአብሔርም በእስራኤል ላይ ተቆጥቶ የይሁዳን መንግሥት ብቻ በመተው እስራኤላውያንን ከፊቱ አስወገደ።


እግዚአብሔር እስራኤላውያንን ሁሉ ተዋቸው፤ ከፊቱም እስኪወገዱ ድረስ በዝባዦች ለሆኑት ጠላቶቻቸው አሳልፎ በመስጠት ቀጣቸው።


ጌታ በባርያዎቹ በነቢያት ሁሉ አማካይነት ባስጠነቀቃቸው መሠረት፥ ከፊቱ እስኪያስወግዳቸው ድረስ በዚያው ቀጠሉበት፤ ስለዚህ የእስራኤል ሕዝብ ከሀገሩ ተማርኮ ወደ አሦር ተወሰደ፤ አሁንም በዚያው ይገኛል።


እግዚአብሔር በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ሕዝብ ላይ ተቆጥቶ ከፊቱ አስወገዳቸው፤ ሴዴቅያስም በባቢሎን ንጉሥ ላይ ዐመፀ።


ቃል ኪዳኑን ለዘለዓለም፥ እስከ ሺህ ትውልድ ያዘዘውን ቃሉን አሰበ፥


ከአብርሃም ጋር ያደረገውን ኪዳን፥ ለይስሐቅም የማለውን፥


ለእነርሱም ኪዳኑን አሰበ፥ እንደ ጽኑ ፍቅሩም ብዛት ተጸጸተ።


ከኃጢአቴ ፊትህን መልስ፥ በደሌንም ሁሉ ደምስስልኝ።


እርሱ ግን ርኅሩኅ ነው፥ በደላቸውንም ይቅር አላቸው፥ አላጠፋቸውምም፥ ከቁጣውም መመለስን አበዛ፥ መዓቱንም ሁሉ አላቃጠለም።


አቤቱ፥ አንተ ግን መሓሪና ርኅሩኅ አምላክ ነህ፥ ለቁጣ የዘገየህ፥ ጽኑ ፍቅርህና እውነትህ የበዛ፥


እርሱም እንዲህ አለው፦ “እኔ መልካምነቴን ሁሉ በፊትህ አሳልፋለሁ የጌታንም ስም በፊትህ አውጃለሁ፤ ይቅር የምለውን ይቅር እላለሁ፥ የምምረውን እምራለሁ።”


ከነቀልኋቸውም በኋላ መልሼ እምራቸዋለሁ፥ እያንዳንዱንም ወደ ርስቱ እያንዳንዱንም ወደ ምድሩ እመልሳለሁ።


ቢያሳዝንም እንደ ምሕረቱ ብዛት ይራራልና፥


እኔም ለያዕቆብ የማልሁትን ቃል ኪዳኔን አስታውሳለሁ፤ እንዲሁም ለይስሐቅና ለአብርሃም የማልሁትንም ቃል ኪዳኔን አስታውሳለሁ፤ ምድሪቱንም አስታውሳለሁ።


ከዚህ በኋላ በግራው ያሉትን ደግሞ እንዲህ ይላቸዋል ‘እናንተ የተረገማችሁ! ከእኔ ወዲያ ራቁ! ለዲያብሎስና ለመላእክቱ ወደ ተዘጋጀው ወደ ዘለዓለም እሳት ሂዱ።


ጌታ ለሕዝቡ ይፈርዳል፥ ለአገልጋዮቹም ያዝናል። ኃይላቸውም እንደደከመ፥ የታሰረም ሆነ የተለቀቀ እንደሌለ ሲያዩ፥


ከጌታ ፊት ከኃይሉም ክብር ርቀው በዘለዓለም ጥፋት ይቀጣሉ።


ከዚያም በመካከላቸው ያሉትን ባዕዳን አማልክት አስወገዱ፤ ጌታንም አመለኩ፤ እርሱም የእስራኤልን መከራ ሊታገሠው የማይቻለው ሆነ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች