2 ነገሥት 10:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)14 ኢዩም “እነዚህን ሰዎች ከነሕይወታቸው ያዙአቸው!” ሲል ለጭፍሮቹ ትእዛዝ ሰጠ፤ ጭፍሮቹም ያዙአቸውና ኢዩ በዚያው በውሃ ጉድጓድ አጠገብ ገደላቸው። ብዛታቸውም በሙሉ አርባ ሁለት ሲሆን፥ ከእነርሱ አንድ እንኳ በሕይወት አልተረፈም። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም14 እርሱም፣ “ከነሕይወታቸው ያዟቸው!” ሲል አዘዘ፤ ስለዚህ ከነሕይወታቸው ወስደው በቤት ኤከድ ጕድጓድ አጠገብ አርባ ሁለቱን ሰዎች ገደሏቸው፤ አንድ እንኳ አላስቀረም። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም14 ኢዩም “እነዚህን ሰዎች ከነሕይወታቸው ያዙአቸው!” ሲል ለጭፍሮቹ ትእዛዝ ሰጠ፤ ጭፍሮቹም ያዙአቸውና ኢዩ በዚያው በውሃ ጒድጓድ አጠገብ ገደላቸው። ብዛታቸውም በሙሉ አርባ ሁለት ሲሆን፥ ከእነርሱ አንድ እንኳ በሕይወት አልተረፈም። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)14 እርሱም፥ “በሕይወታቸው ያዙአቸው” ብሎ አዘዘ። በበግ ጠባቂዎች ቤትም አጠገብ አርባ ሁለቱን ሰዎች ገደሉአቸው፤ ከእነርሱም አንድ ሰው እንኳ አላስቀረም። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)14 እርሱም “በሕይወታቸው ያዙአቸው!” አለ። ያዙአቸውም፤ በበግ ጠባቂዎችም ቤት አጠገብ ባለው ጕድጓድ አርባ ሁለቱን ሰዎች ገደሉአቸው፤ ማንንም አላስቀረም። ምዕራፉን ተመልከት |