Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ቆሮንቶስ 9:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 በእኛ በኩል እግዚአብሔርን የማመስገኛ ምክንያት የሚሆነውን ልግስናችሁ በሁሉ ነገር ባለ ጠጎች ያደርጋችኋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ሁልጊዜ በልግስና መስጠት እንድትችሉ በሁሉ ነገር ያበለጽጋችኋል፤ ልግስናችሁም በእኛ በኩል የሚደርሳቸው ሰዎች እግዚአብሔርን ለማመስገን ምክንያት ይሆናቸዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ልግሥናችሁ በእኛ አማካይነት የሚደርሳቸው ሰዎች ሁሉ እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ዘንድ ሁልጊዜ እንድትለግሡ እግዚአብሔር በሁሉ ነገር ያበለጽጋችኋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ለብዙ ሰዎች ስለ ሰጣ​ች​ሁም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ምስ​ጋና በም​ታ​ደ​ር​ግ​ላ​ችሁ ልግ​ስና ሁሉ ባለ​ጸ​ጎች ትሆ​ና​ላ​ችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 በእኛ በኩል ለእግዚአብሔር የምስጋና ምክንያት የሚሆነውን ልግስና ሁሉ እንድታሳዩ በሁሉ ነገር ባለ ጠጎች ትሆናላችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ቆሮንቶስ 9:11
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከሳዶቅም ወገን የሆነ ታላቁ ካህን ዓዛርያስ፦ “ሕዝቡ ቁርባኑን ወደ ጌታ ቤት ማቅረብ ከጀመረ ወዲህ በልተናል፥ ጠግበናልም፥ ጌታ ሕዝቡን ባርኮአልና ብዙ ተርፎአል፤ የተረፈውም ይህ ክምር ትልቅ ነው” ብሎ ተናገረ።


የራሴ በሆነ ነገር ላይ የወደድሁትን ማድረግ አልችልምን? ወይስ እኔ መልካም ስለ ሆንኩ ትመቀኛለህን?


እንዲሁም ሁለት የተቀበለው ሌላ ሁለት አተረፈ።


ምክር ከሆነ መምከር፤ መስጠት ከሆነ በልግስና መስጠት፤ ማስተዳደር ከሆነ በትጋት ማስተዳደር፤ ምሕረት ማድረግ ከሆነ በደስታ መማር።


በንግግር ሁሉ በእውቀትም ሁሉ በሁሉም ነገር በእርሱ ባለ ጠጎች እንድትሆኑ ተደርጋችኋልና፤


እናንተም ደግሞ ስለ እኛ እየጸለያችሁ ስትደግፉን፤ በብዙዎች ጸሎት ስለ ተሰጠን ስጦታ ብዙ ሰዎች ስለ እኛ ምስጋና ያቀርባሉ።


በብዙዎች በኩል የተትረፈረፈው ጸጋ፥ ለእግዚአብሔር ክብር ምስጋናን እንዲያበዛ፥ ሁሉም ነገር ስለ እናንተ ሆኗል።


ነገር ግን እኔ ለእናንተ ያለኝን በጎ ሐሳብ በቲቶ ልብ ውስጥ ያኖረ አምላክ የተመሰገነ ይሁን፤


ይህም ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን የጌታን የራሱን ክብርና የእኛን በጎ ፈቃድ ለማሳየት በምናገለግለው በዚህ የቸርነት ሥራ ከእኛ ጋር አብሮን እንዲሄድ በአብያተ ክርስቲያናት ተመርጧል።


የዚህ አገልግሎት ረድኤት ለቅዱሳን የሚጎድላቸውን በሙሉ የሚሰጥ ብቻ ሳይሆን ለእግዚአብሔር የሚቀርብ ብዙ ምስጋና ምክንያትም ነው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች