Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ቆሮንቶስ 7:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ይህን የምለው እናንተን ለመኮነን አይደለም፤ በአንድነት ለመሞትና በአንድነት ለመኖር በልባችን ስፍራ እንዳላችሁ አስቀድሜ ተናግሬለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ይህን የምለው ልኰንናችሁ አይደለም፤ ምክንያቱም ከዚህ በፊት እንደ ነገርኋችሁ፣ በልባችን ውስጥ ስፍራ አላችሁ፤ ስለዚህ ብንኖርም ብንሞትም ዐብረን ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ይህንንም የምለው በእናንተ ላይ ለመፍረድ አይደለም። ከዚህ በፊት እንደ ነገርኳችሁ እናንተ በልባችን ውስጥ ናችሁ፤ ስለዚህ በሕይወትም ሆነ በሞት ሁልጊዜ ከእናንተ አንለይም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ይህ​ንም የም​ለው በእ​ና​ንተ ለመ​ፍ​ረድ አይ​ደ​ለም፤ ለሞ​ትም፥ ለሕ​ይ​ወ​ትም ቢሆን እና​ንተ በል​ባ​ችን እን​ዳ​ላ​ችሁ ፈጽሜ ተና​ግ​ሬ​አ​ለ​ሁና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ለኵነኔ አልልም፤ በአንድነት ለመሞትና በአንድነት ለመኖር በልባችን እንዳላችሁ አስቀድሜ ብዬአለሁና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ቆሮንቶስ 7:3
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ስለዚህም እናንተን በፍቅር በመሻት የእግዚአብሔርን ወንጌል ብቻ ሳይሆን የገዛ ነፍሳችንን ደግሞ ለማካፈል በጎ ፈቃዳችን ነበረ፤ ምክንያቱም ለእኛ እጅግ የተወደዳችሁ ሆናችሁ ስለ ነበር ነው።


ከእናንተ ርቄ ሳለሁ እነዚህን ነገሮች የምጽፍላችሁ ወደ እናንተ በምመጣበት ጊዜ ሥልጣኔን በኃይል እንዳልጠቀም ነው፤ ጌታም ይህን ሥልጣን የሰጠኝ እናንተን ለማነጽ እንጂ ለማፍረስ አይደለም።


እኔ ግን ስለ ነፍሳችሁ በብዙ ደስታ ገንዘቤን አወጣለሁ፤ ራሴን እንኳ እከፍላለሁ። ከመጠን ይልቅ ብወዳችሁ፥ የናንተ ፍቅር እንዴት ያንሳል?


ስለምን? ስለማልወዳችሁ ይመስላችኋል? እንደምወዳችሁ እግዚአብሔር ያውቃል።


እንግዲያስ ጽፌው እንኳን ቢሆን ኖሮ፥ ስለ እኛ ያላችሁ ትጋት በእናንተ በኩል በእግዚአብሔር ፊት እንዲገለጥ እንጂ፥ ስለ በደለኛ ወይም ስለ ተበዳይ አይደለም የጻፍኩት።


ሰዎች ሁሉ የሚያውቁትና የሚያነብቡት በልባችን የተጻፈ መልእክታችን እናንተ ናችሁ።


በእስራቴም ወንጌልንም መመከቻና መጽኛ በማድረግ ሁላችሁ ከእኔ ጋር በጸጋ ተካፋዮች ስለ ሆናችሁ፥ በልቤ ትኖራላችሁና ስለ ሁላችሁ ይህን ላስብ ይገባኛል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች