Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ቆሮንቶስ 7:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 በልባችሁ ስፍራ አኑሩን፤ ማንንም አልበደልንም፤ ማንንም አላጭበረበርንም፤ ማንንም መጠቀሚያ አላደረግንም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ልባችሁን አስፉልን፤ እኛ ማንንም አልበደልንም፤ ማንንም ወደ ብልሹነት አልመራንም፤ ማንንም አላታለልንም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ከልባችሁ ተቀበሉን፤ እኛ ማንንም አልበደልንም፤ ማንንም አልጐዳንም፤ ማንንም መጠቀሚያ አላደረግንም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 አሁ​ንም ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ ታገ​ሡን፥ የበ​ደ​ል​ነው የለም፤ የገ​ፋ​ነ​ውም የለም፤ ያጠ​ፋ​ነ​ውም የለም፤ የቀ​ማ​ነ​ውም የለም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 በልባችሁ ስፍራ አስፉልን፤ ማንንም አልበደልንም፥ ማንንም አላጠፋንም፥ ማንንም አላታለልንም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ቆሮንቶስ 7:2
23 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሙሴም እጅግ ተቈጣ፥ ጌታንም እንዲህ አለው፦ “ወደ ቁርባናቸው አትመልከት፤ እኔ ከእነርሱ አንድ አህያ እንኳ አልወሰድሁም፥ ከእነርሱም አንድ ሰው አልበደልሁም።”


ማንም የማይቀበላችሁ ወይም ቃላችሁን የማይሰማ ከሆነ ከዚያ ቤት ወይም ከዚያች ከተማ የእግራችሁን ትቢያ አራግፉችሁ ውጡ።


“እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል፤ እኔንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል።


ወደምትገቡባትም ከተማ ሁሉ ቢቀበሉአችሁ፥ የሚያቀርቡላችሁን ብሉ፤


ከማንም ብር ወይም ወርቅ ወይም ልብስ አልተመኘሁም፤


እንደ እነዚህ ያሉት ሰዎች የገዛ ሆዳቸውን እንጂ ጌታችንን ክርስቶስን አያገለግሉምና፤ በሚያሳምን ንግግርና በሽንገላ የየዋሆችን ልብ ያታልላሉ።


ትምክህታችን ይህ ነው፦ በዚህ ዓለም ይልቁንም በእናንተ ዘንድ፥ በእግዚአብሔር ጸጋ እንጂ በሥጋዊ ጥበብ ባልሆነ፥ በእግዚአብሔር ቅድስናና ቅንነት እንደኖርን፥ የሕሊናችን ምስክርነት ነው።


እንደገና ይህን እላለሁ፥ ማንም ሰው ሞኝ የሆንሁ አይምሰለው፤ እንደ ሞኝ ለሚያስበኝ፥ እኔም በጥቂቱ እንድመካ እንደ ሞኝ ይቀበለኝ።


ከእናንተም ጋር እያለሁ በሚጎድለኝ ጊዜ፥ ከመቄዶንያ የመጡት ወንድሞች የጎደለኝን በሙሉ ስላሟሉልኝ፥ በማንም ላይ ሸክም አልሆንኩም፤ በማንኛውም መንገድ በእናንተ ላይ ሸክም እንዳልሆን ተጠንቅቄአለሁ፤ እጠነቀቅማለሁ።


የሚያሳፍረውን ስውር ነገር ጥለናል፤ በተንኮል አንመላለስም ወይም የእግዚአብሔርን ቃል በውሸት አንቀላቅልም፤ እውነትን በመግለጥ ግን በእግዚአብሔር ፊት ለሰው ሕሊና ሁሉ ራሳችንን እናቀርባለን።


እንግዲህ በሙሉ ደስታ በጌታ ተቀበሉት፤ እርሱን የሚመስሉትንም አክብሩአቸው፤


“ወደ እናንተ ቢመጣ፥ ተቀበሉት፤” የሚል ትእዛዝ የተቀበላችሁለት የበርናባስ የወንድሙ ልጅ ማርቆስ እንዳረገው እንዲሁ አብሮ ከእኔ ጋር የታሰረ አርስጥሮኮስ ሰላምታ ያቀርብላችኋል።


በእናንተ በአማኞች መካከል እንዴት ባለ ቅድስናና ጽድቅ ነቀፋም በሌለበት ኑሮ እንደ ነበርን እናንተና እግዚአብሔር ምስክሮች ናችሁ፤


እርሱን እልከዋለሁ፤ አንተም ልቤ እንደምትቀበል አድርገህ ተቀበለው።


እንግዲህ እንደ ወንድምህ እስከ ቆጠርከኝ ድረስ፥ እንደ እኔ አድርገህ ተቀበለው።


ማንም ወደ እናንተ ቢመጣ ይህንም ትምህርት ባያመጣ በቤታችሁ አትቀበሉት፤ ሰላምም አትበሉት፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች