Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ቆሮንቶስ 1:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 በእርግጥም፥ ሙታንን በሚያነሣ በእግዚአብሔር እንጂ በራሳችን እንዳንታመን፥ የሞት ፍርድ እንደተላለፈብን በውስጣችን ተሰምቶን ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 በርግጥም የሞት ፍርድ እንደ ተፈረደብን ይሰማን ነበር፤ ይህም የሆነው ሙታንን በሚያስነሣ በእግዚአብሔር እንድንታመን እንጂ፣ በራሳችን እንዳንታመን ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 እንዲያውም ሞት እንደ ተፈረደብን ያኽል ተሰምቶን ነበር፤ ይህም ሁሉ የደረሰብን፥ የምንተማመነው ሙታንን በሚያስነሣ በእግዚአብሔር እንጂ በራሳችን ኀይል አለመሆኑን እንድንገነዘብ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ሙታ​ንን በሚ​ያ​ስ​ነ​ሣ​ቸው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንጂ በራ​ሳ​ችን እን​ዳ​ን​ታ​መን በው​ስ​ጣ​ችን ለመ​ሞት ቈር​ጠን ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 አዎን፥ ሙታንን በሚያነሣ በእግዚአብሔር እንጂ በራሳችን እንዳንታመን፥ እኛ ራሳችን የሞትን ፍርድ በውስጣችን ሰምተን ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ቆሮንቶስ 1:9
20 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ብቃታችን ከእግዚአብሔር ነው እንጂ፥ በገዛ እጃችን የሚሆን አንዳችን ነገር ልናስብ እኛ የበቃን አይደለንም፤


እግዚአብሔር ከሙታን እንኳ ሊያስነሣው እንደሚችል አስቦአልና፤ ይስሐቅን እንደ ምሳሌ መልሶ ተቀበለ።


ነገር ግን ይህ ልዩ ኃይል የእግዚአብሄር መሆኑንና ከእኛ አለመመጣቱን ግልጽ ለማድረግ፥ ይህ ሀብት በሸክላ ዕቃ ውስጥ አለን፤


በዚያን ጊዜም ቀኝ እጅህ ልታድንህ እንደምትችል እኔ ደግሞ እመሰክርልሃለሁ።


ጻድቃን ነን በማለት በራሳቸው ለሚታመኑና ሌሎቹን ሁሉ በጣም ለሚንቁ ይህን ምሳሌ ነገራቸው፤


በገዛ ልቡ የሚታመን ሰው ሞኝ ነው፥ በጥበብ የሚመላለስ ግን ይድናል።


እኔ ጻድቁን፦ በእርግጥ በሕይወት ትኖራለህ ባልሁት ጊዜ፥ እርሱ ጽድቁን ተማምኖ ኃጢአት ቢሠራ በሠራው ኃጢአትም ይሞታል እንጂ ጽድቁ አይታሰብለትም።


መንግሥት ለጌታ ነውና፥ እርሱም አሕዛብን ይገዛል።


ኀጥእ በክፋቱ ይደፋል፥ ጻድቅ ግን በእውነቱ ይታመናል።


እኔ፦ በሕይወት ዘመኔ እኩሌታ ከሕይወት ልለይ ይገባልን? በቀረው ዘመኔስ ወደ ሲኦል በሮች መግባት አለብኝን? አልኩ።


ይህም “ስለ አንተ ቀኑን ሙሉ እንገደላለን፤ እንደሚታረዱ በጎች ተቆጠርን፤” ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው።


ወንድሞች ሆይ! በእስያ ስለ ደረሰብን መከራችን ብታውቁት እንወዳለን፤ በሕይወታችን ተስፋ እስክመቁረጥ የሚያደርስ ከዓቅማችን በላይ ያለ ልክ ከብዶብን ነበር።


እርሱ እንዲህ ካለው የሞት አደጋ አድኖናል፤ ያድነናልም፤ ወደፊትም ደግሞ እንደሚያድነን ተስፋችንን በእርሱ ላይ ጥለናል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች