Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ቆሮንቶስ 1:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 መከራ ብንቀበል፥ ስለ መጽናናታችሁና ስለ መዳናችሁ ነው፤ ብንጽናናም፥ እኛ የተቀበልነውን መከራ በመቀበል እናንተም በትዕግሥት መታገስ በመቻላችሁ፥ ስለ መጽናናታችሁ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 መከራ ብንቀበል ስለ እናንተ መጽናናትና መዳን ነው። ብንጽናናም እኛ የተቀበልነውን መከራ በመቀበል በትዕግሥት እንድትጸኑ ስለ እናንተ መጽናናት ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 እኛ መከራ ስንቀበል እናንተ መጽናናትንና መዳንን ታገኛላችሁ፤ እኛ ስንጽናና ደግሞ እናንተም እኛ የምንቀበለውን ዐይነት መከራ በትዕግሥት ተቀብላችሁ ትጽናናላችሁ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 መከራ ብን​ቀ​በ​ልም እና​ንተ እን​ድ​ት​ድ​ኑና እን​ድ​ት​ጽ​ናኑ ነው፤ ብን​ጽ​ና​ናም እኛ የተ​ቀ​በ​ል​ነ​ውን ያን መከራ በመ​ታ​ገሥ ስለ​ሚ​ደ​ረግ መጽ​ና​ና​ታ​ችሁ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ዳሩ ግን መከራ ብንቀበል፥ ስለ መጽናናታችሁና ስለ መዳናችሁ ነው፤ ብንጽናናም፥ እኛ ደግሞ የምንሣቀይበት በዚያ ሥቃይ በመጽናት ስለሚደረግ ስለ መጽናናታችሁ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ቆሮንቶስ 1:6
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ስለዚህ በክርስቶስ ኢየሰሱስ ያለውን መዳን ከዘለዓለም ክብር ጋር እንዲያገኙ ስል ስለ ተመረጡት ደግሞ ሁሉን ነገር እታገሣለሁ።


እኛ በእግዚአብሔር በምንጽናናበት መጽናናት በመከራ ያሉትን ሁሉ ማጽናናት እንድንችል፥ እርሱ በመከራችን ሁሉ ያጽናናናል።


ይህ በጸሎታችሁና በኢየሱስ ክርስቶስ መንፈስ እርዳታ አማካይነት ለመዳኔ እንደሚሆንልኝ አውቄያለሁና፤


ስለዚህ፥ ክብራችሁ ነውና፥ ስለ እናንተ ስለምቀበለው መከራዬ እንዳትታክቱ እለምናችኋለሁ።


ነገር ግን ለዚሁ የሠራን እግዚአብሔር ነው፤ እርሱም የመንፈሱን መያዣ ሰጠን።


እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ ዓላማውም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን።


እኔ ግን ስለ ነፍሳችሁ በብዙ ደስታ ገንዘቤን አወጣለሁ፤ ራሴን እንኳ እከፍላለሁ። ከመጠን ይልቅ ብወዳችሁ፥ የናንተ ፍቅር እንዴት ያንሳል?


ጊዜውንም በፈጸምን ጊዜ ወጥተን ሄድን፤ ሁላቸውም ከሚስቶቻቸውና ከልጆቻቸው ጋር እስከ ከተማው ውጭ ድረስ ሸኙን፤ በባሕሩም ዳር ተንበርክከን ጸለይን፤


አሕዛብ ስለ ሆናችሁ ስለ እናንተ ነው እኔ ጳውሎስ ለክርስቶስ ኢየሱስ እስረኛ የሆንኩት።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች