Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ቆሮንቶስ 1:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ልታነብቡት ወይም ልትረዱት የማትችሉትን የተለየ ነገር አንጽፍላችሁም፥ ሁሉንም እንደምትረዱ ተስፋ አደርጋለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ልታነብቡት ወይም ልትረዱት የማትችሉትን ነገር አንጽፍላችሁም፤ ሁሉንም እንደምትረዱ ተስፋ አደርጋለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 አንብባችሁ ማስተዋል የምትችሉትን ነገር ካልሆነ ሌላ ምንም አንጽፍላችሁም፤ በሙሉ ማስተዋል እንደምትችሉ ተስፋ አደርጋለሁ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 የም​ታ​ነ​ቡ​ት​ንና የም​ታ​ው​ቁ​ትን ነው እንጂ፥ ሌላ የም​ን​ጽ​ፍ​ላ​ችሁ የለ​ምና፥ ይህ​ንም እስከ ፍጻሜ እን​ደ​ም​ታ​ስ​ተ​ው​ሉት ተስፋ አደ​ር​ጋ​ለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13-14 ከምታነቡትና ከምታስተውሉት በቀር ሌላ አንጽፍላችሁምና፤ በጌታችን በኢየሱስ ቀን እናንተ ደግሞ ትምክህታችን እንደምትሆኑ እንዲሁ ትምክህታችሁ እንድንሆን፥ በከፊል ስለ እኛ እንዳስተዋላችሁ ፈጽማችሁ ታስተውሉት ዘንድ ተስፋ አደርጋለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ቆሮንቶስ 1:13
6 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በነጋም ጊዜ ምድሩን አላወቁትም፤ ነገር ግን የአሸዋ ዳር ያለውን የባሕር ሰርጥ ተመለከቱ፤ ቢቻላቸውም መርከቡን ወደዚያ ይገፉ ዘንድ ቆረጡ።


እርሱም ደግሞ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ቀን ያለ ነቀፋ እንድትሆኑ እስከ ፍጻሜ ድረስ ያጸናችኋል።


እኛ ግን የማንበቃ እንዳልሆንን እንደምታውቁ ተስፋ አደርጋለሁ።


የሚያሳፍረውን ስውር ነገር ጥለናል፤ በተንኮል አንመላለስም ወይም የእግዚአብሔርን ቃል በውሸት አንቀላቅልም፤ እውነትን በመግለጥ ግን በእግዚአብሔር ፊት ለሰው ሕሊና ሁሉ ራሳችንን እናቀርባለን።


እንግዲህ የጌታን ፍርሃት አውቀን፥ ሰዎችን ለማስረዳት እንጥራለን፤ ስለ ራሳችን ከሆነ በእግዚአብሔር ዘንድ የተገለጥን ነን፤ ለእናንተም ሕሊና የተገለጥን እንደ ሆንን ተስፋ አደርጋለሁ።


የእምነትህም ኅብረት፥ በእኛ ዘንድ ያለውን በጎ ነገር ሁሉ በማወቅ፥ ለክርስቶስ ኢየሱስ ፍሬ እንዲያፈራ እለምናለሁ፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች