Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ዜና መዋዕል 8:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 የጌታም ሰው ዳዊት እንዲህ አዝዞ ነበርና ካህናቱን እንደ አባቱ እንደ ዳዊት ሥርዓት በየአገልግሎታቸው ሰሞን ከፈላቸው፤ ሌዋውያንም እንደ ሥርዓታቸው እንዲያመሰግኑ፥ በካህናቱም ፊት እንዲያገለግሉ በየሰሞናቸው ከፈላቸው፤ ጠባቂዎችንም ደግሞ በየበሩ ሁሉ በየሰሞናቸው ከፈላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 የአባቱን የዳዊትን ሥርዐት በመከተልም፣ ካህናቱን በየአገልግሎት ክፍላቸው ሌዋውያኑንም ምስጋናውን እንዲመሩና በየዕለቱ ሥራቸው ካህናቱን እንዲረዱ መደባቸው። ደግሞም የእግዚአብሔር ሰው ዳዊት ባዘዘው መሠረት፣ የቤተ መቅደሱን በር ጠባቂዎች በልዩ ልዩ በሮች ጥበቃ ላይ በየክፍላቸው መደባቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 አባቱ ዳዊት የደነገጋቸውን መመሪያዎች በመከተልም የካህናቱንና ካህናቱን በሥራና መዝሙር በመዘመር የሚረዱትን ሌዋውያን የየዕለቱን የሥራ መደብ አቀናበረ፤ እንዲሁም የእግዚአብሔር ሰው ዳዊት ባዘዘው መሠረት የቤተ መቅደሱ ዘበኞች በእያንዳንዱ ቅጽር በር የዕለት ሥራቸውን እንዲያከናውኑ አከፋፍሎ መደበ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰው ዳዊት እን​ዲህ አዝዞ ነበ​ርና ካህ​ና​ቱን እንደ አባቱ እንደ ዳዊት ሥር​ዐት በየ​አ​ገ​ል​ግ​ሎ​ታ​ቸው ሰሞን ከፈ​ላ​ቸው፤ ሌዋ​ው​ያ​ንም እንደ ሥር​ዐ​ታ​ቸው ያመ​ሰ​ግኑ ዘንድ፥ በካ​ህ​ና​ቱም ፊት ያገ​ለ​ግሉ ዘንድ በየ​ሰ​ሞ​ና​ቸው ከፈ​ላ​ቸው፤ በረ​ኞ​ቹ​ንም ደግሞ በየ​በሩ ሁሉ በየ​ሰ​ሞ​ና​ቸው ከፈ​ላ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 የእግዚአብሔርም ሰው ዳዊት እንዲህ አዝዞ ነበርና ካህናቱን እንደ አባቱ እንደ ዳዊት ሥርዓት በየአገልግሎታቸው ሰሞን ከፈላቸው፤ ሌዋውያንም እንደ ሥርዓታቸው ያመሰግኑ ዘንድ፥ በካህናቱም ፊት ያገለግሉ ዘንድ በየሰሞናቸው ከፈላቸው፤ በረኞቹንም ደግሞ በየበሩ ሁሉ በየሰሞናቸው ከፈላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ዜና መዋዕል 8:14
33 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በርም ጠባቂዎች ሰሎም፥ ዓቁብ፥ ጤልሞን፥ አሒማን፥ ወንድሞቻቸውም ነበሩ፤ ሰሎምም አለቃ ነበረ።


ወንድሞቹም ሸማዕያ፥ ዓዛርኤል፥ ሚላላይ፥ ጊላላይ፥ መዓይ፥ ናትናኤል፥ ይሁዳና ሐናኒ የእግዚአብሔር ሰው የዳዊትን የዜማ መሣሪያ ይዘው ሄዱ፤ ጸሐፊው ዕዝራም በፊታቸው ነበረ።


የሌዋውያኑ መሪዎች ሐሻብያ፥ ሼሬብያ፥ የቃድሚኤል ልጅ ኢያሱና ወንድሞቻቸው ደግሞ ከፊት ለፊታቸው ሆነው የእግዚአብሔር ሰው ዳዊት በሰጠው ትእዛዝ መሠረት ክፍል በክፍል ትይዩ ሆነው ያወድሱና ያመሰግኑ ነበር።


በሙሴም መጽሐፍ በተጻፈው መሠረት በኢየሩሳሌም ባለው በእግዚአብሔር አገልግሎት ላይ ካህናቱን በየማዕረጋቸው ሌዋውያኑንም በየክፍላቸው መደቡአቸው።


ዳዊትም በራሱ ዘመን የእግዚአብሔርን አሳብ ካገለገለ በኋላ አንቀላፋ፤ ከአባቶቹም ጋር ተጨምሮ መበስበስን አየ፤


እርሱንም ከሻረው በኋላ ዳዊትን በእነርሱ ላይ እንዲነግሥ አስነሣው፤ ሲመሰክርለትም ‘እንደ ልቤ የሆነ ሰው ፈቃዴንም ሁሉ የሚያደርግ የእሴይን ልጅ ዳዊትን አገኘሁ፤’ አለ።


እርሱም በክፍሉ ተራ በእግዚአብሔር ፊት በክህነት ሲያገለግል፥


በይሁዳ ንጉሥ በሄሮድስ ዘመን ከአብያ ክፍል የሆነ ዘካርያስ የሚባል አንድ ካህን ነበረ፤ ሚስቱም ከአሮን ሴት ልጆች ወገን ነበረች፤ ስምዋም ኤልሳቤጥ ነበረ።


አገልግሎቱም በተዘጋጀ ጊዜ ካህናቱም በስፍራቸው፥ ሌዋውያኑም በየክፍላቸው እንደ ንጉሡ ትእዛዝ ቆሙ።


ሕዝቅያስም የካህናትንና የሌዋውያንን ሰሞን በየክፍላቸውና በየአገልግሎታቸው አቆመ፤ በጌታ ቤት አደባባይ በሮች የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የአንድነቱን መሥዋዕት እንዲያቀርቡ፥ እንዲያገለግሉ፥ እንዲያመሰግኑም ክብርም እንዲሰጡ ካህናቱንና ሌዋውያኑን አቆመ።


የምታደርጉት ይህ ነው፤ በሰንበት ቀን ከምትገቡት ከእናንተ ከካህናትና ከሌዋዊውያን ከሦስቱ አንዱ በመግቢያ በሮች ላይ ጠባቂዎች ሁኑ፤


ካህናቱም ከመቅደሱ በወጡ ጊዜ ሁሉም ተቀድሰው ነበር፥ በሰሞናቸውም አልተከፈሉም ነበር፤


ዳዊትም፦ “የሥራውን ሁሉ ንድፈ ሐሳብ እንዳውቅ ይህ ሁሉ በጌታ እጅ ተጽፎ መጣልኝ” አለ።


ዳዊትም በሸመገለ ጊዜ፥ ዕድሜንም በጠገበ ጊዜ ሰሎሞንን በእስራኤል ላይ አነገሠው።


ከእነርሱም ጋር ካህናቱ ከፍ አድርገው ለማሰማት መለከትና ጸናጽል ለእግዚአብሔርም መዝሙራት የዜማ ዕቃ ይዘው ነበር፤ የኤዶታምም ልጆች ጠባቂዎች ነበሩ።


ኢዮርብዓም መሥዋዕት ለማቅረብ በመሠዊያው አጠገብ ቆሞ ሳለ በጌታ ትእዛዝ የተላከ አንድ ነቢይ እነሆ ከይሁዳ መጥቶ እዚያ ደረሰ፤


“የጌታ መንፈስ በእኔ ተናገረ፤ ቃሉም በአንደበቴ ነው።


የጌታ ሰው ሙሴ ከመሞቱ በፊት የእስራኤልን ሕዝብ የባረከበት ቃለ ቡራኬ ይህ ነው።


እንዲሁም ንጉሥ ዳዊት በየቀኑ እንደሚገባቸው በታቦቱ ፊት ዘወትር እንዲያገለግሉ አሳፍንና ወንድሞቹን፥ ዖቤድ-ኤዶምንም፥ ስልሳ ስምንቱንም ወንድሞቻቸውን በዚያ በጌታ ቃል ኪዳን ታቦት ፊት ተዋቸው።


የአሮንም ልጆች አመዳደብ ይህ ነው። የአሮን ልጆች ናዳብ፥ አብዩድ፥ አልዓዛር፥ ኢታምር ነበሩ።


ዳዊትና የሠራዊቱ አለቆችም ከአሳፍና ከኤማን ከኤዶታም ልጆች በመሰንቆና በበገና በጸናጽልም ትንቢት የሚናገሩትን ሰዎች ለማገልገል ለዩ፤ በአገልግሎታቸውም ሥራ ይሠሩ የነበሩት ሰዎች ቍጥር ይህ ነበረ።


የደጁም ጠባቂዎች ምድባቸው እንደዚህ ነበር፤ ከቆሬያውያን ከአሳፍ ልጆች የቆሬ ልጅ ሜሱላም።


እነርሱም ንጉሡ ስለ ነገሩ ሁሉና ስለ መዝገቡ ካህናቱንና ሌዋውያኑን ያዘዘውን ነገር ሁሉ አልተላለፉም።


ይህንም ትእዛዝ ጌታ በነቢያቱ እጅ አዝዞአልና እንደ ዳዊትና እንደ ንጉሡ ባለ ራእይ እንደ ጋድ፥ እንደ ነቢዩም እንደ ናታን ትእዛዝ፥ ጸናጽልና በገና መሰንቆም አስይዞ ሌዋውያንን በጌታ ቤት አቆመ።


የእስራኤልም ንጉሥ ዳዊትና ልጁም ሰሎሞን እንደ ጻፉት በየሰሞናችሁና በየአባቶቻችሁ ቤቶች ራሳችሁን አዘጋጁ፤


በአራቱ ማዕዘኖች፥ በምሥራቅ፥ በምዕራብ፥ በሰሜን፥ በደቡብ፥ ጠባቂዎች ነበሩ።


ዳዊትም ከአልዓዛር ልጆች ከሳዶቅ ጋር፥ ከኢታምርም ልጆች ከአቢሜሌክ ጋር ሆኖ እንደ አገልግሎታቸው ሥርዓርት ከፍሎ መደባቸው።


በማናቸውም ነገር ሁሉ ርኩስ የሆነ ሰው እንዳይገባ በጌታ ቤት በር በጠባቂዎችን አኖረ።


የአሳፍም ልጆች መዘምራን እንደ ዳዊት፥ እንደ አሣፍም እንደ ኤማንም የንጉሡም ባለ ራእይ እንደነበረው እንደ ኤዶታም ትእዛዝ በየስፍራቸው ነበሩ፤ የደጁም ጠባቂዎች በሮቹን ሁሉ ይጠብቁ ነበር፤ ወንድሞቻቸውም ሌዋውያን ያዘጋጁላቸው ነበርና ከአገልግሎታቸው እንዲርቁ አያስፈልጋቸውም ነበር።


ማታንያ፥ ባቅቡቅያ፥ አብድዩ፥ ምሹላም፥ ጣልሞን፥ ዓቁብ በበሮቹ አጠገብ የሚገኙትን ዕቃ ቤቶች የሚጠብቁ በር ጠባቂዎች ነበሩ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች