Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ዜና መዋዕል 7:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ጌታም ለሰሎሞን በሌሊት ተገልጦ እንዲህ አለው፦ “ጸሎትህን ሰምቻለሁ፥ ይህንም ስፍራ ለራሴ ለመሥዋዕት ቤት መርጫለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 እግዚአብሔር ለሰሎሞን በሌሊት ተገልጦለት እንዲህ አለው፤ “ጸሎትህን ሰምቻለሁ፤ ይህንም ስፍራ መሥዋዕት የሚቀርብበት ቤተ መቅደስ እንዲሆን ለራሴ መርጬዋለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 እግዚአብሔር በሌሊት ተገልጦለት እንዲህ አለው፤ “ጸሎትህን ሰምቼአለሁ፤ ይህን ቤተ መቅደስ ለእኔ መሥዋዕት የሚቀርብበት ስፍራ ይሆን ዘንድ መርጬዋለሁ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለሰ​ሎ​ሞን በሌ​ሊት ተገ​ልጦ እን​ዲህ አለው፥ “ ጸሎ​ት​ህን ሰም​ቻ​ለሁ፤ ይህ​ንም ስፍራ ለራሴ ለመ​ሥ​ዋ​ዕት ቤት መር​ጫ​ለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 እግዚአብሔርም ለሰሎሞን በሌሊት ተገልጦ እንዲህ አለው “ጸሎትህን ሰምቻለሁ፤ ይህንም ስፍራ ለራሴ ለመሥዋዕት ቤት መርጫለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ዜና መዋዕል 7:12
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በዚያም ሌሊት ጌታ፦ “እንድሰጥህ የምትፈልገውን ነገር ጠይቀኝ” ሲል ለሰሎሞን ተገለጠ።


እግዚአብሔር ከዚህ በፊት በገባዖን እንደ ተገለጠለት አሁንም እንደገና ተገለጠለት።


አብራምም የዘጠና ዘጠኝ ዓመት ሰው በሆነ ጊዜ ጌታ ለአብራም ተገለጠለትና፦ “እኔ ኤልሻዳይ ነኝ፥ በፊቴ ተመላለስ፥ ፍጹምም ሁን፥


አሁንም ስሜ ለዘለዓለም በዚያ እንዲኖር ይህን ቤት መርጫለሁ ቀድሻለሁም፤ ዐይኖቼና ልቤም ዘወትር በዚያ ይሆናሉ።


ጌታ አምላካችሁም ለስሙ ማደሪያ እንዲሆን ወደ መረጠው ስፍራ፥ እኔ የማዝዛችሁን ሁሉ፥ የሚቃጠሉ መሥዋዕቶቻችሁን ሌሎች መሥዋዕቶቻችሁን፥ አሥራቶቻችሁንና የእጃችሁን ስጦታ፥ እንዲሁም ለጌታ የተሳላችሁትን ምርጥ ነገሮች ሁሉ ወደዚያ ታመጣላችሁ።


‘ቆርኔሌዎስ ሆይ! በእግዚአብሔር ፊት ጸሎትህ ተሰማ ምጽዋትህም ታሰበ።


መልአኩ ግን እንዲህ አለው፦ “ዘካርያስ ሆይ! ጸሎትህ ተሰምቶልሃልና አትፍራ፤ ሚስትህ ኤልሳቤጥም ወንድ ልጅ ትወልድልሃለች፤ ስሙንም ዮሐንስ ብለህ ትጠራዋለህ።


ስለዚህ እግዚአብሔር ሰማኝ፥ የልመናዬን ድምፅ አደመጠ።


ጌታ ሆይ የምስኪኖችን ምኞት ሰማህ፥ ልባቸውንም ታጸናለህ፥ ጆሮህንም ታዘነብላለህ፤


“ሕዝቤን ወደሚመራው ወደ ንጉሥ ሕዝቅያስ ተመልሰህ በመግባት እንዲህ በለው፦ ‘እኔ የቀድሞ አባትህ የዳዊት አምላክ እግዚአብሔር ጸሎትህን ሰምቻለሁ፤ እንባህንም ተመልክቻለሁ፤ እኔ እፈውስሃለሁ፤ ከሦስት ቀንም በኋላ ወደ ቤተ መቅደስ ትወጣለህ፤


ከዚህም በኋላ ኤልያስ ኤልሳዕን፥ “እነሆ! አንተ በዚህ ቆይ፤ እኔ ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ እንድሄድ እግዚአብሔር አዞኛል” አለው። ኤልሳዕ ግን “እኔ በሕያው እግዚአብሔር ስም እምልልሃለሁ! ከቶ ከአንተ አልለይም!” ሲል መለሰለት፤ ስለዚህም አብረው ጉዞአቸውን ቀጠሉ።


በቤተ መቅደሱም ውስጥ የአሼራን ምስል አኖረ፤ ይህም ቤተ መቅደስ እግዚአብሔር ለዳዊትና ለልጁ ለሰሎሞን “ይህ በኢየሩሳሌም የሚገኘው ቤተ መቅደስ እኔ ለዘለዓለም እመለክበት ዘንድ ከዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች ግዛት ሁሉ የመረጥኩት ስፍራ ነው፤


በዚያ ጊዜ የይሁዳና የኢየሩሳሌም ቁርባን እንደ ዱሮው ዘመንና እንደ ቀደሙት ዓመታት ጌታን ደስ የሚያሰኝ ይሆናል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች