2 ዜና መዋዕል 5:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)6 ንጉሡም ሰሎሞን ከእርሱም ጋር የተሰበሰቡ የእስራኤል ማኅበር ሁሉ በታቦቱ ፊት ሆነው ከብዛታቸው የተነሣ የማይቈጠሩትንና በቍጥር የማይለኩትን በጎችና በሬዎች ይሠዉ ነበር። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም6 ንጉሥ ሰሎሞንና ዐብሮት በዚያ የተሰበሰበው መላው የእስራኤል ጉባኤ ስፍር ቍጥር የሌላቸውን በጎችና በሬዎች በታቦቱ ፊት ሠዉ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም6 ንጉሥ ሰሎሞንና ሕዝቡ ሁሉ በቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት ለፊት ተሰበሰቡ፤ ከዚህም በኋላ ከብዛታቸው የተነሣ ሊቈጠሩ የማይችሉ እጅግ ብዙ በጎችንና የቀንድ ከብቶችን መሥዋዕት አድርገው አቀረቡ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)6 ንጉሡም ሰሎሞንና የእስራኤል ማኅበር ሁሉ፥ እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሁሉ በአንድነት በታቦቷ ፊት ሆነው ከብዛት የተነሣ የማይቈጠሩትንና የማይመጠኑትን በጎችና በሬዎች ይሠዉ ነበር። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)6 ንጉሡም ሰሎሞን ከእርሱም ጋር የተሰበሰቡ የእስራኤል ማኀበር ሁሉ በታቦቱ ፊት ሆነው ከብዛት የተነሣ የማይቈጠሩትንና የማይመጠኑትን በጎችና በሬዎች ይሠዉ ነበር። ምዕራፉን ተመልከት |