Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ዜና መዋዕል 4:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 አሥሩንም ገበታዎች ሠርቶ አምስቱን በቀኝ አምስቱን በግራ በመቅደስ ውስጥ አኖራቸው። አንድ መቶም የወርቅ ድስቶች ሠራ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ዐሥር ጠረጴዛ ሠርቶም ወደ ቤተ መቅደሱ በማስገባት ዐምስቱን በስተ ደቡብ፣ ዐምስቱን ደግሞ በስተሰሜን በኩል አኖራቸው፤ ደግሞም አንድ መቶ ጐድጓዳ የወርቅ ሳሕኖች ሠራ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 እንዲሁም ዐሥር ጠረጴዛዎችን አሠርቶ በቤተ መቅደሱ ዋና ክፍል ውስጥ አምስቱን በሰሜን፥ አምስቱን በደቡብ በኩል አኖራቸው፤ በተጨማሪም አንድ መቶ ማንቈርቈሪያዎችን ከወርቅ አሠራ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ዐሥ​ሩ​ንም የወ​ርቅ ገበ​ታ​ዎች ሠርቶ አም​ስ​ቱን በቀኝ፥ አም​ስ​ቱ​ንም በግራ በመ​ቅ​ደሱ ውስጥ አኖ​ራ​ቸው። አንድ መቶም የወ​ርቅ ጽዋ​ዎ​ችን ሠራ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ዐሥሩንም ገበታዎች ሠርቶ አምስቱን በቀኝ፥ አምስቱን በግራ በመቅደስ ውስጥ አኖራቸው። አንድ መቶም የወርቅ ድስቶች ሠራ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ዜና መዋዕል 4:8
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ለጌታ ቤት አገልግሎት ይውሉ ዘንድ ሰሎሞን የሚከተሉትን ዕቃዎች አሠራ፤ እነርሱም የወርቁ መሠዊያ፥ ለእግዚአብሔር የሚቀርበው ኅብስት ማኖሪያ የወርቅ ጠረጴዛ።


ሰሎሞንም በጌታ ቤት የነበረውን ዕቃ ሁሉ፥ የወርቁንም መሠዊያ፥ የተቀደሰውንም ኅብስት የሚቀመጥባቸውን ገበታዎች ሠራ፤


የሠራዊት ጌታም ለሕዝብ ሁሉ በዚህ ተራራ ላይ ታላቅ የሰባ ግብዣ፥ ያረጀ የወይን ጠጅ፥ ቅልጥም የሞላባቸው የሰቡ ነገሮች፥ መልካምና የበሰለ የወይን ጠጅ ግብዣ ያደርጋል።


ወደ መቅደሴም ይገባሉ እኔን ለማገልገል ወደ ገበታዬ ይቀርባሉ ሥርዓቴን ይጠብቃሉ።


በዚያ ቀን በፈረሶች ሻኩራ ላይ፦ “ለጌታ የተቀደሰ” ተብሎ ይጻፋል። በጌታም ቤት ያሉ ምንቸቶች በመሠዊያው ፊት እንዳሉ ዳካዎች ይሆናሉ።


እናንተ ግን፦ “የጌታ ገበታ የረከሰ ነው፤ ፍሬውና ምግቡም የተናቀ ነው በማለታችሁ አረከሳችሁት።


የጌታን ጽዋና የአጋንንትን ጽዋ ልትጠጡ አትችሉም፤ ከጌታ ማዕድና ከአጋንንት ማዕድ ልትካፈሉ አትችሉም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች